ለዩኒቨርሲቲው መምህራን ለ3 ተከታታይ ቀናት ሲሰጥ የቆየው የE-Learning ስልጠና በስኬት ተጠናቀቀ

ትምህርት ሚኒስቴር ከአሪዞና ስቴት ዩኒቨርሲቲ፣ ማስተር ካርድ ፋውንዴሽን እና ሻያሾኔ ድርጅቶች ጋር በመተባበር እየተገበረ ያለው የe-SHE ፕሮጀክት ለመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በE-Learning የተያዘው ዕቅድ ተግባራዊ ለማድረግ ለራያ ዩኒቨርሲቲ መምህራን ከህዳር 18-20/ 2017 ዓ.ም ለተከታታይ 3 ቀናት ሲሰጥ የቆየው የE-Learning ስልጠና በስኬት ተጠናቋል።
ስልጠናው በዋናነት ራያ ዩኒቨርሲቲ በ “E-Learning የMasterclass Training” እና “Student Success Suite” እየተሰጠ ያለውን ሥልጠና ተግባራዊ ለማድረግ፣ አጠናክሮ ለማስቀጠል እንዲሁም ለመምህራን የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር ለመተግበር ያለመ ነበር።
የራያ ዩኒቨርሲቲ የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ፣ የሕግ ትምህርት ቤት፣ የቢዝነስና ኢኮኖሚክስ፣ የግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት፣ ተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ፣ የህክምና እና ጤና ሳይንስ፣ የኢንጅነሪንግና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ መምህራን ስልጠናውን ወስደዋል።
ዶ/ር ንጉሥ መሰለ፤ በ E-Learning ትግበራ ዙርያ የአካዳሚክ ጉዳዮች፣ የ E-Learning ዳይሬክተር እና አስተባባሪዎች፣ ኮሌጅ ዲኖች፣ ዲፓርትመንቶች፣ የ ICT ባለሙያዎች እና አስተባባሪዎች ሚና ዝርዝር ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
መ/ር መሰለ ብርሃኑ በበኩላቸው “E-Learning የMasterclass Training” እና “Student Success Suite” ሥልጠናዎች ለመተግበር የዩኒቨርሲቲዎች ሚና ዝርዝር ገለፃ አድርገዋል።
ሰልጣኝ መምህራን እንደተናገሩት ስልጠናው በE-Learning ዲጂታላይዜሽን ትግበራ እና የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ ወሳኝ ነው ብለዋል።
በስልጠናው መዝጊያ መርሃ-ግብር ሰልጣኝ መምህራን የተለያዩ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች ያነሱ ሲሆን በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ማብራሪያ እና ምላሽ ተሰጥቶ ተጠናቋል።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ህዳር 21/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
**************************************