ራያ ዩኒቨርሲቲ ለተቀበላቸው የ1ኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች የህይወት ክህሎት ስልጠና ሰጠ

በራያ ዩኒቨርሲቲ ማህበራዊ እና ስነ-ሰብ ኮሌጅ የተዘጋጀ የህይወት ክህሎት ስልጠና ለ1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ መርሃ ግብር ተማሪዎች ህዳር 11/ 2017 ዓ.ም ተሰጠ።
ስልጠናው በዋናነት የህይወት ክህሎት ምንነት እና ጠቀሜታ፣ ራስን ማወቅ (Self Awareness) ፣ ስለራስ የተስተካከለ ግምት መያዝ (Self Esteem)፣ በራስ መተማመን (Self Confidence)፣ ውጤታማ የጊዜ አጠቃቀም (Time Management)፣ ውጤታማ የአጠናን ዘዴ (Effective Study Strategies)፣ ብዝሐነት እና አብሮ የመኖር እሴት (Multiculturalism and Adaptation) እንዲሁም ማህበራዊ ትስስር እና መልካም የስነ ምግባር መርሆች ትኩረት ያደረገ ነበር፡፡
ስልጠናውን በዩኒቨርሲቲው ማህበራዊ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ ስር የሚገኙ የስነ-ልቦና (Psychology) እና ስነ-ማህበረሰብ (Sociology) መምህራን ተሰጥቷል፡፡
ሰልጣኝ ተማሪዎች በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀላቸው የህይወት ክህሎት ስልጠና ጠቃሚ ግንዛቤ የተገኘበት በመሆኑ ስልጠናው ቀጣይነት ሊኖረው ይገባል በማለት አስተያየታቸውን አክለዋል፡፡
********************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሕዳር 12 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
********************************************