ራያ ዩኒቨርሲቲ ለዛታ ወረዳ የትምህርት መርጃ መጻሕፍት ድጋፍ ማበርከቱን ተገለጸ

በመማር ማስተማር፣ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ከፍተኛ እምርታ እያስመዘገበ ያለው ራያ ዩኒቨርሲቲ ቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች ዕቅዱን መሰረት በማድረግ በተለያየ የክፍል ደረጃዎች ለሚገኙ ተማሪዎች፣ መምህራን እና የትምህርት ቤት ማህበረሰብን የሚያገለግሉ የትምህርት መርጃ መጻሕፍት በበደቡባዊ ትግራይ ዞን ለሚገኝ ዛታ ወረዳ ድጋፍ አድርጓል፡፡
በድጋፍ ርክክቡ ተገኘተው መልዕክት ያስተላለፉት የዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር መምህር ደባሲ ግደይ፤ ዩኒቨርሲቲው የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እና በዞኑ የሚገኙ ትምህርት ቤቶች ጤናማ እና ስልታዊ የትምህርት ሂደት እንዲኖራቸው በማድረግ ተማሪዎች በዕውቀት፣ ክህሎት እና ስነ ምግባር ለማብቃት ድጋፉ ትልቅ ፋይዳ አለው ብለዋል፡፡
የደቡባዊ ትግራይ ዞን ትምህርት ዘርፍ አስተባባሪ የሆኑት መምህር ሰማን ሞላ በበኩላቸው፤ ራያ ዩኒቨርሲቲ አዲስ ዩኒቨርሲቲ ቢሆንም በዞኑ የትምህርት ጥራትን ለማረጋገጥ እያደረገ ያለው እንቅስቃሴ የሚደነቅ ነው በማለት የዚህም ማሳያ በጦርነቱ ምክንያት ትልቅ የትምህርት ጉዳት ለደረሰበት ዛታ ወረዳ የትምህርት መርጃ መጻሕፍት ድጋፍ ማድረጉን እና ከዩኒቨርሲቲው ጋር የበለጠ ተቀራርቦ በመስራት ተማሪዎቻቸውንና መምህራኖቻቸውን ለመጥቀም እንዲህ ዓይነት ድጋፎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ መልእክታቸውንም አስተላልፈዋል፡፡
በመጨረሻም በእለቱ የተገኙት ተወካዮች እንደተናገሩት ይህ የተደረገላቸው ድጋፍ በወረዳው ለሚገኙት ትምህርት ቤቶች ትልቅ ጠቀሜታ ያለው መሆኑን ገልፀው ለተደረጋላቸው ድጋፍ ዩኒቨርሲቲውን በማመስገን ከዩኒቨርሲቲው ጋር ያላቸውን ግንኙነት ወደፊም አጠናክረው እንደሚቀጥሉ ገልፀዋል።
*******//***********************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ መጋቢት 22/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*******//*********************************