የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሠላም ሚኒስቴር ከመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ጋር በመተባበር የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በ2016 ዓ.ም በሃገር ግንባታ ዙርያ ያበረከቱት አስተዋጽኦ ለመገምገም ዛሬ ታኅሣሥ 18 /2017 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አዩ ኢንተርናሽናል ሆቴል ባዘጋጀው የውይይት መድረክ ራያ ዩኒቨርሲቲ ላበረከተው ትልቅ አሥተዋጽኦ ከሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ የእውቅና እና የምሥጋና ምሥክር ወረቀት ተበርክቶለታል።
የእውቅና እና የምሥጋና ምስክር ወረቀቱን የዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንቶች ተሳታፊዎች የነበሩ ሲሆን የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) ዛሬ ታኅሣሥ 18 /2017 ዓ.ም በተቀበሉበት ወቅት በሠጡት አስተያየት ራያ ዩኒቨርሲቲ የሠላም አምባሳደር ለመሆን እና ሃገራዊ እንዲሁም ዓለም አቀፋዊ ግዴታውን ለመወጣት ሥራውን አጠናክሮ ይቀጥልበታል ብለዋል።
በእውቅና እና ሽልማት ስነ-ሥርዓቱ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በ2016 ዓ.ም በሃገር ግንባታ ዙርያ በተለይ የግንዛቤ ማስጨበጫ ሥልጠናዎች በመሥጠት እና በማስተባበር ትልቅ አሥተዋጽኦ ማድረጋቸውን ተገልጿል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታኅሣሥ 18 /2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ
*********//*****************************