ራያ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ የሃገራችን ክፍሎች በተላያየ ምክንያት ከቄያቸው ተፈናቅለው በመቐለ IDP Center ተጠልለው ለሚገኙ ተፈናቃዮች እና በርዕደ መሬት ምክንያት ከቀያቸው ለተፈናቀሉ የገቢ ረሱ ዞን አዋሽ ፈንታሌ እና ዱለቻ ወረዳ ነዋሪዎች የቁሳቁስ ድጋፍ አድርጓል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ድጋፉን ለመቐለ ከተማ አሥተዳደር ከንቲባ የማህበራዊ ጉዳይ አማካሪ አቶ ጌቱ ሃይሉ እና የአፋር ብሄራዊ ክልላዊ መንግስት ላቋቋመው የድጋፍ አሰባሳቢ ግብረሃይል አስረክበዋል፡፡