ራያ ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊውን የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን አጠናቅቆ የ2017 ዓ.ም የዓቅም ማሻሻያ የትምህርት መርኃ ግብር (Remedial Program) ተማሪዎቹን በተሳካ መንገድ እየተቀበለ ይገኛል።

በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምኅርት ሚኒስቴር በ2017 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ ለመማር የተመደቡ የዓቅም ማሻሻያ የትምኅርት መርኃ ግብር (Remedial Program) ተማሪዎች ከዛሬ ሐሙስ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው እየገቡ እና እየተመዘገቡ ይገኛሉ።
በቅበላው መርኃ ግብር የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት፣ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ የተማሪዎች ህብረት፣ ሰራተኞች እና የማኅበረሠብ ካውንስል አባላት ለተማሪዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ አቀባበል እያደረጉላቸው ይገኛል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ሐሙስ ጥር 15 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
**************************************