ራያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለሚወስዱ የመደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች የሞዴል መውጫ ፈተና ሰጠ።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ጥር /2017 ዓ.ም የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለሚወስዱ የመደበኛ እና ኢ-መደበኛ ተማሪዎች ከዚህ ቀደም የተመዘገበውን ውጤት ለማስጠበቅ እና በቀጣይ የተሻለ ውጤት ለማስመዝገብ ለ 78 ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው መምህራን በበለፀገ ሲስተም ሞዴል መውጫ ፈተና በዩኒቨርሲቲው የፈተና ማእከል ህዳር 30/ 2017 ዓ.ም ተሰጥቷል።
የሞዴል መውጫ ፈተናውን የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛና መካከለኛ አመራሮች በቦታው ተገኝተው የተመለከቱት ሲሆን የዩኒቨርሲቲው የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ ምክትል ፕረዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በሰጡት ማብራሪያ መሰረት ሞዴል ፈተናው ተማሪዎች ከሲስተሙ ጋር በማላመድ ለዋናው መውጫ ፈተና (Exit Exam) ለማዘጋጀት የራስ መተማመን ለማሳደግ እና ጥሩ ውጤት እንዲያስመዘግቡ ያስችላል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው የፈተናዎች ማስተባበሪያ ማእከል ዳይሬክተር መ/ር ተስፋይ ሃረገወይን እንደገለፁት፤ ጥሩ ውጤት የሚመዘገበው በተማሪዎች የግል ጥረትና በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የጋራ ጥረት በመሆኑ ሁሉም የድርሻውን እየተወጣ ይገኛል በማለት አስተባባሪው ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ሲስተሙን ላበለፀጉት እና ለሚቆጣጠሩት፣ ፈተናውን ላወጡት እና ላስተባበሩት መምህራን እና ላብ ቴክኒሻኖች አመስግነዋል።
ሞዴል ፈተና የወሰዱት ተማሪዎች በበኩላቸው በዩኒቨርሲቲው የተሰጣቸው ሞዴል መውጫ ፈተና እጅግ መደሰታቸውን ገልፀው ፈተናው ውጤታማና የተሳካ እንደነበር እና ለዋናው መውጫ ፈተና እንዲዘጋጁ ትልቅ ዓቅም እንደፈጠረላቸው ሃሳባቸውን ገልፀዋል።
************//**************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታህሳስ 01/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*********//******************************