ራያ ዩኒቨርሲቲ የአንበጣ መንጋ፣ ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እና የምርት ብክነትን አስቀድሞ መከላከል የሚያስችል እና በዞኑ የኢኮኖሚ ዘርፍ የሚመራ ግብረ ሃይል ለማቋቋም ከትግራይ ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ እና ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ዛሬ ጥቅምት 09/2017 ዓ/ም በመኾኒ ከተማ የምክክር መድረክ አካሄደ።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ እንደተናገሩት በምግብ ዋስትና ራሳችን ለመቻል ምርትና ምርታማነት ለማሻሻል አዳዲስ የቴክኖሎጂ አማራጮችን በመጠቀም ብክነትን መቀነስ ያስፈልጋል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው የምርምር ጉዳዮች ዓለም አቀፍ አጋርነት አስተባባሪ ዶ/ር ገሰሰ ንጉስ ባቀረቡት ፅሁፍ የአንበጣ መንጋ ሊያስትለው የሚችል ጉዳትና ስጋት ምርትን በአግባቡ እንዴት መሰብሰብ እንደሚቻል ገለፃ አድርገዋል።
የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክተር መ/ር ደባሲ ግደይ የአንበጣ መንጋ፣ ወቅቱ ያልጠበቀ ዝናብ እና የምርት ብክነት ለመከላከል ምን መደረግ እንዳለበት ገለፃ አድገዋል።
ዶ/ር እያሱ አብርሃ በበኩላቸው ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ፣ የአንበጣ መንጋና የምርት ብክነት የሚያስከትለው አሉታዊ ተፅእኖ እና እንዴት መከላከል እንደሚቻል ሰነዳዊ ፅሁፍ አቅርበዋል።
በምክክር መድረኩ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የዘርፉ ባለሙያዎች፣ የትግራይ ግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ቢሮ ሃላፊ ዶ/ር እያሱ አብርሃ፣ የደቡባዊ ትግራይ ዞን እና ወረዳ አመራሮች እና ባለሙያዎች የተሳተፉ ሲሆን የሚመራ የሚያስተባብር ግብረ ሃይል እንደሚቋቋም ለማወቅ ተችሏል።
********************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
**************************************