ራያ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም የዓቅም ማሻሻያ የትምህርት መርኃ ግብር (Remedial Program) ተማሪዎቹን ለመቀበል ዝግጅቱን አጠናቆ በመጠባበቅ ላይ ነው- ዶ/ር ነጋ ዓፈራ

ራያ ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊውን የትምህርት ግብአት፣ የተማሪዎች መማሪያ ክፍል፣ መኝታ፣ ምግብና፣ ሕክምና፣ እና ሌሎች አገልግሎቶች እና የመሠረተ ልማት ሥራዎቹን አጠናቆ ጥር 15 እና 16 /2017 ዓ.ም የ2017 ዓ.ም የዓቅም ማሻሻያ የትምህርት መርኃ ግብር (Remedial Program) ተማሪዎቹን ለመቀበል በመጠባበቅ ላይ መሆኑን የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማኅበረሠብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ነጋ ዓፈራ ለዩኒቨርሲቲው የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ ጽ/ቤት አገልግሎት ገልጸዋል።
ምክትል ፕረዚደንቱ አክለው እንደገለጹት በዩኒቨርሲቲው የተመደቡት የዓቅም ማሻሻያ የትምህርት መርኃ ግብር (Remedial Program) ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ዋና ሬጂስትራር ጽሕፈት ቤት በአካል ተገኝተው እንዲመዘገቡ እና ትምህርታቸውን መከታተል እንዳለባቸው መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታኅሣሥ 30/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ
************************************