በራዩ የተለያዩ የማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖጂ ሽግግር የፕሮጀክት ንድፈ ሀሳቦች ለግምገማ ቀረቡ፡፡

በዩኒቨርሲቲው የማህበረሰብ ቁጠባዊ፣ ማህበራዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች እና ተግዳሮቶች ችግር የሚፈቱ፣ ህይወትን የሚለውጡ፣ ፍላጎቶችን የሚያሟሉ፣ ስነ-ምህዳር የሚጠብቁ፣ ፈጠራን የሚያበረታቱ፣ ማህበራዊ ግዴታን የሚያጠናክሩ እንዲሁም ማህበረሰብን የሚያስተሳስሩ እና እሴትን የሚያጠናክሩ ስምንት (😎 የማህበረሰብ አገልግሎት እና ሶስት (3) የቴክኖጂ ሽግግር በጠቅላላ አስራ አንድ (11) ፕሮጀክቶች ንድፈ ሀሳብ በሚመለከታቸው ባለሙያዎች ሚያዝያ 03/2016 ዓ/ም ግምገማ ተደረገላቸው።
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) በግምገማው ዕለት ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር በዩኒቨርሲቲው የሚሰሩ የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ስራዎች የማህበረሰቡን ችግር ለመፍታት ትኩረት ያደረጉ በሳይንሳዊ፣ በተቀናጀ አሰራር እና ተጠያቂነት በመከተል የበኩሉን አስተዋጽኦ ማድረግ አለበት ብለዋል።
ለግምገማ የቀረቡ የምርምር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት እና ቴክኖሎጂ ሽግግር ፕሮጀክቶች የማህበረሰቡን የድህረ ጦርነት ማህበራዊ፣ ቁጠባዊ፣ ከባቢያዊ እና ስነ-ልቦናዊ ችግሮች በሀገር በቀል እውቀቶች እና የምርምር ውጤቶች ለመፍታት እንዲሁም ዩኒቨርሲቲው ከማህበረሰቡ ጋር ያለው ግንኙነት የሚያጠናክሩ ናቸው፡፡
**********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሚያዝያ 04/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
ለበለጠ መረጃ