በራያ ዩኒቨርሲቲ ለ2017 ዓ.ም 1ኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎች መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት (DOCO) በድምቀት ተጀመረ።

ራያ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ.ም 1ኛ ዓመት አዲስ ገቢ ተማሪዎቹን ህዳር 09 እና 10 /2017 ዓ.ም ተቀብሎ የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕረዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር)፣ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱን ጨምሮ ዲኖች፣ ዳይሬክተሮች እና አስተባባሪዎች በተገኙበት የ2017 ዓ.ም 1ኛ ዓመት የቅድመ ምረቃ ተማሪዎች ዛሬ ሰኞ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት (DOCO) በድምቀት ተጀመረ።
መምህራን እና ተማሪዎች በተመደቡበት ክፍል በሰዓታቸው ተገኝተው መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደቱን ተጀምሯል።

የዩኒቨርሲቲው አመራር፣ መምህራን እና ተማሪዎች ላደረጉት ውጤታማ ቅንጅት ዩኒቨርሲቲው ምስጋናውን ያቀረባል።


ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ህዳር 16 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
****************************************