የራያ ዩኒቨርሲቲ ቤተ- መጻሕፍትና ዶክመንቴሽን ዳይሬክቶሬት ከብሄራዊ ቤተ-መፃህፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ ጋር በመተባበር በተለያየ ደረጃ ለሚገኙ የቤተ-መጻሕፍት ቤተ-መዛግብት ሰራተኞች የመሰረታዊ ቤተ መጻሕፍት ሳይንስ እና ዲጂታላይዜሽን ስልጠና ከዛሬ ጥቅምት 20/2017 ዓ/ም ጀምሮ እየተሰጠ ይገኛል፡፡
የስልጠናው ቁልፍ ዓላማ አዳዲስ የቤተ-መጽሐፍትና ቤተ-መዛግብት እውቀት፣ ቴክኖሎጂዎችና ዲጂታላይዜሽን ስርዓት ትግበራ ለማረጋገጥ ነው፡፡
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕረዚደንት ተወካይ ቀሲስ ንጉስ መሰለ (ዶ/ር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ስልጠናው ጥራት ያለው የቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት አገልግሎት ለመስጠትና የሰራተኞቻችን ዓቅም ለማሳደግ አስፈላጊ በመሆኑ ሰልጣኞች የሚሰጠውን ስልጠና በንቃት በመሳተፍ የሚጠበቀውን እውቀትና ልምድ በመቅሰም በስራ ቦታ እንዲያውሉ ሃሳባቸውን ገልፀዋል፡፡
የራያ ዩኒቨርሲቲ ቤተ መፃህፍት እና ቤተ መዛግብት ዳይሬክተር መ/ር ተኽሉ ሃ/ኪሮስ ባደረጉት ንግግር ለአስር ተከታታይ ቀናት የሚሰጥ ስልጠና የሰራተኞቻችን ዓቅምና ልዩ ችሎታ ለማሳደግ እንዲሁም መልካም የስራ አካባቢ ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ ይኖረዋል ብለዋል፡፡
ስልጠናውን ከኢትዮጵያ ብሄራዊ ቤተ-መጻሕፍትና ቤተ-መዛግብት ኤጀንሲ የመጡ ባለሙያዎች አቶ እስራኤል ብዙ እና አቶ ስለሺ ወርቁ እየሰጡ ይገኛሉ፡፡
**************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ጥቅምት 20 ቀን 2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
****************************************