በራያ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ የተመራ ልኡክ ቡድን በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ስራዎች ጎብኝተዋል።

በራያ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ የተመራ ልኡክ ቡድን በዩኒቨርሲቲው እየተሰሩ ያሉ የተለያዩ ስራዎች ጎብኝተዋል።
******************
የተከበሩ አቶ ካሁን ጎፌ (የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ንግድና ቀጠናዎች ትስስር ሚኒስቴር ዲኤታና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ)፣ የተከበሩ ፕሮፌሰር መንገሻ አድማሱ (የፕሮፌሰሮች ካውንስል አባልና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል)፣ የተከበሩ ዶ/ር እያሱ በርሀ (የትግራይ ግብርና እና ገጠር ልማት ቢሮ ሀላፊ የራያ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ አባል)፣ የተከበሩ አቶ ሀፍቱ ኪሮስ (የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል)፣ ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ (የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት እና የሥራ አመራር ቦርድ ፀሀፊ) እንዲሁም የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አሠራሮች በዩኒቨርሲቲው ማህበረብ ደማቅ አቀባበል ተደረገላቸው።
የሥራ አመራር ቦርዱ በተማሪዎች መመገብያ አዳራሽ ተገኝተው ከተማሪዎች ጋር ምሳ በልተዋል።
በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ ግንባታዎች፣ የእንስሳት እርባታ እና ማድለብ ስራዎች፣ ከእንጨት ፍጆታ ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የተቀየረ የተማሪዎች ምግብ መስሪያ መሽኖች፣ የተማሪዎች መኝታ፣ ጎብተኝተዋል።
የሥራ አመራር ቦርዱ የዩኒቨርሲቲውን የ 2016 ዓ/ም የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት በጥልቀት ተወያይቶ ለሚቀጥሉት 6 ወራት ዩኒቨርሲቲው ሊሰራቸው የሚገባቸው ስትራቴጂያዊ ስራዎች የትኩረት አቅጣጫዎች አስቀምጧል።
በመጨረሻም መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ከሥራ አመራር ቦርድ አባላት ጋር የተደረገ ውይይት የመምህራን መኖርያ ችግር፣ የስርቪስ እጥረት፣ የ2014 ዓ/ም የደሞዝ ይከፈለን ጥያቄ፣ የኑሮ ውድነት ችግር፣ የኑሮ ውድነት ችግር፣ የመምህራን ፕሮሞሽን ችግር፣ የተማሪዎች ቀለብ ችግር የሥራ አመራር ቦርዱ አባላት ማይጨው ሰማእታት አዳሪ ትምህርት ቤት ይገነባል፣ የመምህራን ፕሮሞሽን በሀገር አቀፍ ደረጃ መከልከሉን፣ በግብርና ስራዎች ዩኒቨርሲቲው ጠንክሮ መስራት እንዳለበት ማብራርያ ሰጥተዋል። በሌላ በኩል የትግራይ ደቡባዊ ዞን አስተዳደር ለዩኒቨርሲቲው 10 ሄክታር የምርምር ቦታ ሰጥቷል።
******************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ጥር 07/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
********************
???
ድረ ገፅ: www.rayu.edu.et

Loading