በራያ ዩኒቨርሲቲ የተሰሩ ዘመናዊ የበግ ማድለብያ ሼዶች ተመረቁ።

ዩኒቨርሲቲው የግብርና እና ተፈጥሮ ሃብት ስራዎቹን ለማዘመን እና ማህበረሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ የተለያዩ ስራዎች እየሰራ መሆኑን የሚታወቅ ሲሆን 500 በጎች ለማድለብ የሚያገለግሉ ሁለት ዘመናዊ ሼዶች በትግራይ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፣ የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ሃፍቱ ኪሮስ፣ የትግራይ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ከላሊ አድሀና እና የራዩ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ዛሬ ሚያዝያ 19/2016 ዓ/ም በድምቀት ተመርቀዋል።
በምረቃ ስነ ስርዓቱ የራዩ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር እያሱ ያዘው፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ተከስተ ብርሃኑ፣ የትግራይ ደቡባዊ ዞን ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ሀገር ሽማግሌዎች፣ ሀይማኖት መሪዎች እና ሚድያ አካላት ተገኝተዋል።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ ዩኒቨርሲቲው ያስገነባቸው ሁለቱም ዘመናዊ የበግ ማድለብያ ሼዶች ለበጎቹ አስፈላጊውን እንክብካቤ ለማድረግ፣ በሰዓቱ ምግብ እና ውሃ ለመስጠት፣ ጤንነታቸው ለመከታተል ስለሚረዳ ጥራታቸው የጠበቁ የተለያዩ የበግ ዝርያዎች በተመጣጣኝ ዋጋ ለገበያ በማቅረብ የማህበረሰቡን ፍላጎት ለማሟላት እና የውስጥ ገቢ ለማሳደግ ትልቅ አስተዋፅኦ አለው ብለዋል።
አቶ ሃፍቱ ኪሮስ በምረቃ ስነ ስርዓቱ ባስተላለፉት መልእክት መሰረት ዩኒቨርሲቲው በእንስሳት እርባታ፣ በግቢ ውበት፣ በአዝርእት ማፍራት፣ ቱሪዝም ልማት እና ሌሎች የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ውጤታማ እንቅስቃሴ በማድረግ ማህበረሰቡን ለማገልገል እየሰራ ይገኛል ብለዋል።
**************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሚያዝያ 19/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ
**********************
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇