በትግራይ ክልል ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ የተመራ የልኡክ ቡድን አባላት በዩኒቨርሲቲው የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አካሄዱ።

ዩኒቨርሲቲው ፅዱ፣ ውብ፣ አረንጓዴ እና ማራኪ ግቢ ለማድረግ ከሚሰሩ ውጤታማ ስራዎች መካከል የችግኝ ተከላ መርሀ ግብር አንዱ ሲሆን በትግራይ ኮሙኒኬሽን ፅ/ቤት ሃላፊ አቶ ረዳኢ ሓለፎም፣ የትግራይ ደቡባዊ ዞን ዋና አስተዳዳሪ እና የዩኒቨርሲቲው ስራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ሃፍቱ ኪሮስ፣ የትግራይ ሳይንስ እና ቴክኖሎጂ ፅ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ከላሊ አድሀና እና የራዩ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የተለያየ ጠቀሜታ ያላቸው የማንጎ፣ አፕል፣ ፓፓዬ፣ አቮካዶ እና ሌሎች አትክልቶች የመትከል መርሃ ግብር ዛሬ ሚያዝያ 19/2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው አስጀምረዋል።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብር የራዩ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር እያሱ ያዘው፣ የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ተከስተ ብርሃኑ፣ የትግራይ ደቡባዊ ዞን ማህበረሰብ ተወካዮች፣ ሀገር ሽማግሌዎች፣ ሀይማኖት መሪዎች፣ እና ሚድያ አካላት ተገኝተዋል።
**************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሚያዝያ 19/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ
**************************
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇