የህዳር አክሱም ፅዮን በዓል ምክንያት በማድረግ በአክሱም ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በራያ፣ መቐለ፣ ዓዲ ግራት እና አክሱም ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ከህዳር 17-20/ 2017 ዓ.ም ሲካሄድ የቆየው የእግር ኳስ እና መረብ ኳስ ውድድር ፍፃሜውን አግኝቷል።
በዚህ ውድድር መቐለ ዩኒቨርሲቲ የመረብ ኳስ፣ አክሱም ዩኒቨርሲቲ ደግሞ የእግር ኳስ ዋንጫ ተሸላሚዎች በመሆን ውድድራቸውን አጠናቋል።
በመዝጊያው መርሃ ግብር የአክሱም ዩኒቨርሲቲ አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር አብርሃም ነጋሽ እንደተናገሩት ይህ ውድድር መዘጋጀቱ በዩኒቨርሲቲዎቹ መካከል ያለውን ትልቅ ወዳጅነት የሚፈጥር በመሆኑ ቀጣይነት ባለው ትኩረት ተሰጥቶት ሊሰራ ይገባል ብለዋል።
የውድድሩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው ይህ ውድድር በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ያለውን ትስስር እና አንድነት ለማጠናከር ትልቅ አስተዋፅኦ ስላለው በቀጣይ ተጠናክሮ እንዲቀጥል የሁሉም ድርሻ ሊሆን ይገባል በማለት አስተያየታቸውን አክለዋል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ህዳር 21 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************************