በራያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 የትምህርት ዘመን ከየትምህርት ክፍሉ እጅግ የላቀ የትምህርት አፈፃፀም እና ብቃት ላስመዘገቡ ተማሪዎች ለማበረታታት እና በተማሪዎች ዘንድ መልካም የትምህርት ፉክክር እንዲኖር ለማድረግ የሽልማት እና እውቅና መርሃ ግብር ህዳር 28/2017 ዓ.ም ተካሄደ።
በመርሃ ግብሩ ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለተሸላሚ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ራያ ዩኒቨርሲቲ በሃገራችን ከሚገኙ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል በትምህርት ጥራት ቀዳሚ ደረጃ ላይ የሚገኝ ሲሆን ለዚህ ማሳያም በ2016 ዓ.ም በተከታታይ ሁለት ጊዜ የመውጫ ፈተና አስፈትነን ከኢትዮጵያ 1ኛ ደረጃ ይዘን አጠናቅቀል ብለዋል።
ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በንግግራቸው እንደገለፁት፤ ይህ ትልቅ ውጤት እንደሚዘገብ ደከመኝ ሰለቸኝ ሳይሉ ለሚሰሩ መምህራንን በማመስገን ዩኒቨርሲቲው የላቀ የትምህርት ውጤት ያመጡ ተማሪዎች በየሰሚስተሩ ወይ በየዓመቱ ማበረታታት ለነገ ውጤት አስፈላጊ ስለሆነ አጠናክሮ ስለሚቀጥልበት ተማሪዎች በትላንት ወይ ዛሬ ባገኛችሁት ውጤት ብቻ ሳትዘናጉ ለቀጣይ ከዚህ የበለጠ የትምህርት ብቃት ማስመዝገብ ይኖርባቹኋል በማለት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
እጅግ የላቀ የትምህርት አፈፃፀም ያስመዘገቡ ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲው ዋና ረጂስትራር ዳይሬክተር መምህር አብርሃ ተካ እየተጠሩ ከፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ፣ የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ እና ኮሌጅ ዲኖች የገንዘብ እና ምስክር ወረቀት ሽልማታቸው ተቀብለዋል።
ተሸላሚ ተማሪዎች በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀላቸው የእውቅና እና ሽልማት መርሃ ግብር መደሰታቸውን ገልፀው ለቀጣይም ለበለጠ ውጤት እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ህዳር 29/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************************