በዩኒቨርሲቲው የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና ቅድመ ዝግጅት ግምገማ እና ምልከታ ተደረገ።

ከሰኔ 14-21/2016 ዓ/ም ለሚሰጠው የከፍተኛ ትምህርት የመውጫ ፈተና በዩኒቨርሲቲው የተሰሩ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ከትምህርት ሚኒስቴር የመጡ ተወካይ አቶ ዳመና ሞረዳ፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና የፈተናው ግብረሃይል በጋራ በመሆን ዛሬ ሰኔ 13/2016 ዓ/ም ግምገማ እና ምልከታ አድርገዋል።
የዩኒቨርሲቲው አካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ በዩኒቨርሲቲው ለመጀመሪያ ጊዜ የሚሰጠውን የመውጫ ፈተና በተሳካ ሁኔታ እንዲጠናቀቅ የተሰሩ ዘርፈ ብዙ የቅድመ ዝግጅት ስራዎች ገለፃ አድርገዋል።
የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ዳመና ሞረዳ የመውጫ ፈተናው መመርያ እና በመውጫ ፈተናው ወቅት ሊደረጉ የሚገባቸው ተግባራት ለዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ የመውጫ ፈተና ግብረ ሃይል አባላት እና ተፈታኝ ተማሪዎች ማብራርያ ሰጥተዋል።
የመውጫ ፈተና አስፈፃሚ ግብረ ሀይል አባላት እና ተማሪዎች በበኩላቸው የተለያዩ ሀሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች አንስተው የትምህርት ሚኒስቴር ተወካይ አቶ ዳመና ሞረዳ እና ዶ/ር ነጋ ዓፈራ ምላሽ እና ማብራርያ ሰጥተዋል፡፡
******************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሰኔ 13/2016 ዐዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙየት ሥራ አስፈፃሚ
*************************************
ለበለጠ መረጃ
👇👇👇