በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ምግብ መስሪያ አገልግሎቶች ከማገዶ ወደ ኤሌክትሪክ አገልግሎት ተቀየሩ።

በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ምግብ መስሪያ አገልግሎቶች ማለትም ምጣድ፣ ወጥ መስሪያ፣ ሻይ ማፍያ፣ የእቃ ማጠብያ፣ የዳቦ መጋገርያ፣ ሽንኩርትና ቲማቲም መክተፍያ መሽኖች ሙሉ በሙሉ ወደ ኤሌክትሪክ አገልግሎቶች በመቀየራቸው የተማሪዎች ምግብ በጥራት፣ ጉልበት እና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ አገልግሎት እንዲቀርብ አስችሏል።
ይህ ፕሮጀክት በዩኒቨርሲቲው አቅም የተሰራ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው ለማገዶ የሚያወጣውን አላስፈላጊ ወጪ በመቀነስ፣ ፅዱና አረንጓዴ አከባቢን በመፍጠር ረገድ እንዲሁም በቴክኖሎጂ ሽግግር ዘርፍ ከፍተኛ ውጤት የታየበት ስራ ነው።
የኤሌክትሪክ እንጀራ ቤቱ በፊት ከነበሩ 30 አዳዲስ ምጣዶች ተጨምረውበት አገልግሎቱ ፅዱ እና ጥራት ያለው እንዲሆን አስችሏል።
የኤሌክትሪክ ወጥ ቤቱ ደግሞ ዘመናዊ መሽኖች በመጠቀም የተማሪዎች የተለያዩ የወጥ ዓይነቶች በቀላሉ እና ጊዜ ቆጣቢ በሆነ መንገድ ለመስራት አስችሏል።
በሌላ በኩል የኤሌክትሪክ ሻይ ማፍያ መሽኖቹ በአጭር ሰዓት እና በሚፈለገው መጠን የተማሪዎች ሻይ አፍልተው እንዲያቀርቡ ተደርገው ተሰርተዋል።
የኤሌክትሪክ ሽንኩርትና ቲማተም መክተፍያ መሽኖች ደግሞ የተፈለገውን የሽንኩርትና ቲማቲም መጠን በጥራት ለመክተፍ ይረዳል።
የኤሌክትሪክ ዳቦ መጋገርያ መሽኖቹ ከመጀመርያ እስከ መጨረሻ የዳቦ ስራ ሂደቶች በመሽኑ ስለሚሰራ ጊዜና ጉልበት ከመቆጠቡም ባሻገር ለተማሪዎች ጥራት ያለው ዳቦ እንዲቀርብ ትልቅ አስተዋፅኦ አድርጓል።
በፕሮጀክቱ ውጤታማ ስራ የአደጋ ተጋላጭነት ስጋት ያስቀረ እና ሰራተኞቹ ስራቸውን ያለ ስጋት በጥራት እንዲሰሩ ያስችላል።
*******************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
********************
👇👇👇
ፌስ ቡክ: https://www.facebook.com/Raya University
ድረ ገፅ: www.rayu.edu.et