በዩኒቨርሲቲው “የዓድዋ ድል ለዘላቂ ሠላም እና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል ውይይት ተካሄደ።

128ኛ የዓድዋ ድል በዓል ምክንያት በማድረግ በዩኒቨርሲቲው “የዓድዋ ድል ለዘላቂ ሠላም እና ለጠንካራ ሀገረ መንግስት ግንባታ” በሚል መሪ ቃል የውይይት መድረክ በዩኒቨርሲቲው የክሊኒክ አዳራሽ ዛሬ የካቲት 08/2016 ዓ/ም ተካሄደ።
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ [ፕሮፌሰር] በመክፈቻ ንግግራቸው የዓድዋ ድል የሁሉም ኢትዮጵያዊ ዜጋ የድል ተምሳሌት ስለሆነ ዘላቂ ሠላም እና ጠንካራ ሀገረ መንግስት ለመመስረት የስብእና ግንባታ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ሀገራዊ ማንነት፣ እሴት እና ጥቅም ለማረጋገጥ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ወሳኝ ሚና ይኖርባቸዋል ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ የታሪክ እና ቅርስ አስተዳደር ትምህርት ክፍል መምህራን የሆኑት መምህር ካሕሱ ታደሰ እና መምህር ጎይትኦም አንገሶም በጥናታዊ ፅሑፋቸው ከዓድዋ ድል በፊት የሀገር ድንበር ለማስከበር የተካሄዱ ጦርነቶች እና የተገኙ ስኬቶች፣ የዓድዋ ጦርነት መንስኤዎች፣ ሂደቶች እና ድሉ ለሀገራችን ያስገኘው ጠቀሜታ የሚሉ አጀንዳዎች አቅርበዋል።
በውይይት መድረኩ የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች የተሳተፉ ሲሆን ተሳታፊዎች የዓድዋ ድል ለሀገራችን እድገት ወሳኝ ሚና ስላለው የሚመለከተውን ታሪክ ለሚመለከተው አካል ክብርና ዋጋ በመስጠት የሀገራችን ታሪክ አያያዝ ስርዓት ማጠናከር አለብን ብለዋል።
ከተሳታፊዎቸች ለተነሱ ሀሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በመምህራን ማብራርያ እና ምላሽ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ባደረጉት የመዝግያ ንግግር በሀገራችን ሰላም ለማስፈን ሁላችንን የበኩላችንን ሚና መጫወት አለብን ብለዋል።
****************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
የካቲት 08/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
****************
ለበለጠ መረጃ