ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መጡበት አከባቢ እየተሸኙ ነው።

በራያ ዩኒቨርሲቲ ከሀምሌ 02-12/2016 ዓ.ም ሲሰጥ የቆየው የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና በስኬት መጠናቀቁ የሚታወስ ሲሆን ተፈታኝ ተማሪዎች ወደ መጡበት አከባቢ ዛሬ ጥዋት ሀምሌ 12/2016 ዓ/ም እየተሸኙ ነው ።
በሽኝት ስነ ስርዓቱ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት መሰረት የፈተና ሂደቱ የተሳካ እንዲሆን ዩኒቨርሲቲው አስፈላጊውን ቅድመ ዝግጅት ያደረገ ሲሆን ፈተናውን በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ የፈተና አስፈፃሚ አካላት እንዲሁም ተፈታኝ ተማሪዎች በቆይታቸው ላሳዩት መልካም ስነ ምግባር ዩኒቨርሲቲው ምስጋናውን ያቀርባል ብለዋል።
በዩኒቨርሲቲው በመጀመርያ ዙር 2433 የማህበራዊ ሳይንስ፣ በሁለተኛ ዙር ደግሞ 1820 የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች የ12ኛ ክፍል መልቀቅያ እና የከፍተኛ ትምህርት መግቢያ ፈተና ወስደዋል፡፡
በመጨረሻም ዩኒቨርሲቲው ለተፈታኝ ተማሪዎች ጥሩ ውጤት እንዲያመጡ እና የሰላም ጉዞ እንዲሆንላቸው መልካም ምኞቱን ይገልፃል፡፡
*****************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሀምሌ 12/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
****************************************