“ከእንግዲህ ወደ ኋላ መመለስ ወይም መቆም አይቻልም!!!”

“ከእንግዲህ ወደ ኋላ መመለስ ወይም መቆም አይቻልም!” በሚል መሪ ቃል የዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ/ም የሥራ ዕቅድ አፈፃፀምና በ2017 ዓ/ም ዓመታዊ ዕቅድ ትግበራ ትኩረት ያደረገ የምክክር መድረክ ዛሬ ሀምሌ 18/2016 ዓ.ም ከዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች ጋር ተካሄደ።
በምክክር መድረኩ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ራያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ/ም በተለይ በመማር ማስተማር ሂደቱ ለሌሎች የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት አርአያ የሚሆኑ ውጤታማ ስራዎች በቅንጅት ሰርቷል በማለት ይህ ስኬት እንዲመዘገብ የዩኒቨርሲቲው መምህራን ላደረጉት ርብርብ አመስግነዋል።
ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በንግግራቸው ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ/ም ውጤታማ ስራ ለመስራት እና ከደረስንበት ከፍታ ላለመውረድ እያንዳንዱ የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ ራዕይ (Perception)፣ ቅድመ ዝግጅት (Preparation)፣ ተግባር ተኮር አፈፃፀም (Performance)፣ ምርታማነት (Productivity) እና ጽናት (Perseverance) ማቀናጀት ይጠበቅበታል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ተወካይ መ/ር ብርሃነ ፀጋይ (ረዳት ፕሮፌሰር) የምክክር መድረኩ ዓላማ ሲያብራሩ ዩኒቨርሲቲያችን ያስመዘገበው ዘርፈ ብዙ ውጤት ለማስቀጠል እንደ ራያ ዩኒቨርሲቲ “ከእንግዲህ ወደ ኋላ መመለስ ወይም መቆም አይቻልም!” በማለት በዩኒቨርሲቲው በተካሄደ የስትራቴጂክ ጉዳዮች ክትትል እና ድጋፍ መሰረት በ2017 ዓ/ም ዕቅዶቻችን በቁልፍ የአፈፃፀም አመላካቾች (Key Performance Indicators) እና ሊለኩ የሚችሉ መሆን እንዳለባቸው አብራርተዋል።
የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሃ/ኪሮስ ከበደ በበኩላችወ የዩኒቨርሲቲው ተልዕኮ፣ራዕይና እሴቶች፣ መሪ ቃል፣ አራቱም መነፅሮች (መማርና እድገት፣ የውስጥ አሰራር፣ ፋይናንስና ደንበኞች)፣ ጠንካራ ጎኖች፣ የነበሩ ክፍተቶች፣ የተወሰዱ መፍትሄዎች እንዲሁም የክትትልና ግምገማ ስርዓት ያካተተ የ2016 ዓ/ም ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም እና የ2017 እቅዱ መነሻ ሁኔታዎች፣ ስትራቴጅካዊ ዕይታዎች፣ ቁልፍና ዓበይት ተግባራት፣ ግቦችና ትኩረት የሚሹ ዝርዝር ተግባራት፣ ሊያጋጥሙ የሚችሉ ስጋቶችና መፍትሔዎቻቸው፣ የዕቅድ አፈፃፀም ምእራፎች (የዝግጀት፣ ትግበራ እና የማጠቃለያ ምዕራፍ)፣ የአፈፃፀም ክትትልና ግምገማ ሥርዓት፣ የዕቅድና ሪፖርት ግንኙነትና ፍሰት፣ የማስፈፀሚያ ስልት፣ የክትትል፣ የቁጥጥርና ድጋፍ ሥርኣት እንዲሁም የ2017 ዓ/ም ዕቅድ መተግበርያ መርሃ ግብር የያዘ የ2017 ዓ/ም የሥራ ዕቅድ በዝርዝር አቅርበዋል፡፡
በውይይት መድረኩ በዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች የተመራ የ2016 ዓ/ም ዓመታዊ የሥራ ዕቅድ አፈፃፀም፣ የ2017 በጀት ዓመት ዕቅድና ቁልፍ መካከለኛ ውጤቶች ከተሳታፊዎች ጋር ውይይት የተካሄደ ሲሆን የ2017 ዓ/ም የየዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እና ስትራቴጂክ ጉዳዮች ዓመታዊ ዕቅድ ክለሳ ተደርጓል።
በመጨረሻም ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ባደረጉት የመዝግያ ንግግር ሁሉም የዩኒቨርሲቲው ሰራተኛ የዩኒቨርሲቲው ራእይና ተልእኮ እንዲሳካ በ2017 ዓ/ም ውጤታማ ስራ መስራት ይጠበቅበታል ብለዋል።
****************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሀምሌ 18/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
****************************************