የራያ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ከ USAID/OTI ESP ጋር በመተባበር “የደቡባዊ ዞን ሃገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎች (አቦ ገረብ እና ዱባርተ) ትስስር ማጠናከር!” በሚል መሪ ቃል ውይይት አካሄደ፡፡

የራያ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ከ USAID/OTI ESP ጋር በመተባበር “የደቡባዊ ዞን ሃገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎች (አቦ ገረብ እና ዱባርተ) ትስስር ማጠናከር!” በሚል መሪ ቃል ከደቡባዊ ትግራይ ዞን ማይጨው እና እንዳ መኾኒ ወረዳዎች የመጡ የሃገር ሽማግሌዎች ጋር መስከረም 14/2017 ዓ/ም በማይጨው ከተማ ውይይት ተካሄደ፡፡
USAID/OTI ESP ን በመወከል አቶ ሲሳይ ብሩክ የውይይቱ ዓላማ ሲያብራሩ የህዝባችን ሰላምና ደህንነት ለማረጋገጥና በማህበረሰቡ ዘንድ መልካም ግንኙነት እንዲፈጠር ሃገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎች (አቦ ገረብ እና ዱባርተ) ትስስር ለማጠናከር ያለመ ነው ብለዋል፡፡
የራያ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ዲን መ/ር መሓመድ ባዩ ከተሳታፊዎች ጋር ባደረጉት ውይይት የሃገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎች (አቦ ገረብ እና ዱባርተ) መልካም ተሞክሮዎች፣ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮች እና መፍትሄዎቻቸውን በዝርዝር ተነስቷል፡፡
የማይጨው እና እንዳ መኾኒ ወረዳዎች የሃገር ሽማግሌዎች ካነሷቸው ሀሳቦች መካከል የፍርድ ቤቶች እና የሃገር ሽማገሌዎች ግንኙነት ማጠናከር፣ የተቋማቱ የቁሳቁስ፣ መጓጓዣ፣ ፋይናንስ፣ እና ሰው ሃይል ችግር፣ በዞኑ የሚገኙ የሃገር ሽማግሌዎች ወጥ የሆነ የአሰራር ስርዓት አለመኖሩ፣ የግጭት መንስኤዎች ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ መጠናት እንዳለባቸው፣ ቅድመ፣ ሂደት እና ድህረ የግጭት አፈታት ዘዴዎች ስልጠና እንዲሰጥ፣ የግጭት አፈታት ስርዓት፣ የዞኑ የሃገር ሽማግሌዎች አጋር አካላት፣ ሁሉም የማህበረሰብ ክፍል ያካተተ ስልጠና ቢሰጥ፣ የፍርድ ቤት ውሳኔ መጓተት ለሃገር ሽማግሌዎች የሚፈጥሮውን ተፅዕኖ፣ ሃገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎች (አቦ ገረብ እና ዱባርተ) ትስስር እንዲሁም የመረጃ አያያዝ ስርዓት ዋናዋናዎቹ ናቸው፡፡
በመጨረሻም ከውይይቱ ለመገንዘብ እንደተቻለው ሃገር በቀል የግጭት አፈታት ዘዴዎች (አቦ ገረብ እና ዱባርተ) ትስስር ማጠናከር በማህበረሰቡ ዘንድ የሚታዩ ግጭቶች ለማስወገድ፣ የፍትህ መዛባት እንዲቀረፍና የህዝብ ተጠቃሚነት እነዲረጋገጥ የሁሉም አካላት ቅንጅት ያስፈልጋል፡፡
********************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ መስከረም 14/2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*******************************************