እንኳን ደስአለን
በፌዴራል የፍትሕና ሕግ ኢንስቲትዩት፣ የሕግ ትምህርት ቤቶች ኮንሰርቲየም እና የኢትዮጵያ ሕግ ትምህርት ቤቶች ማህበር በጋራ በአዘጋጁት የእውቅና እና የሽልማት ፕሮግራም የራያ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት በ2016 ዓ/ም በሕግ ትምህርት የመውጫ ፈተና የተፈተኑትን ተማሪዎች በማሳለፍ በሀገር ደረጃ 2ኛ በመውጣት የዋንጫ እና የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሸላሚ ሆኗል።
ሽልማቱን የተቀበሉት የራያ ዩኒቨርሲቲ ሕግ ትምህርት ቤት ዲን መ/ር መሐመድ ባዩ ባስተላለፉት መልእክት፤ የሕግ ትምህርት ቤቱ በሀገር አቀፍ ደረጃ ይህን ሽልማት መቀዳጀቱን የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን እና ሰራተኞች ለትምህርት ጥራት ትኩረት ሰጥተው መስራታቸውን የሚያሳይ መሆኑን ገልፀዋል።
መ/ር መሐመድ አክለው፤ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች ለትምህርት ቤቱ የሚሰጡትን ድጋፍ አመስግነው የመማር ማስተማር ሂደቱን ውጤታማ እንቅስቃሴ በምርምር እና ማሕበረሰብ አገልግሎት ዘርፉም እንደሚደግሙት መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
እንደሚታወቀው የሕግ ትምህርት ቤቱ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ የንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር እና የራያ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ ክቡር ዶ/ር ካሣሁን ጎፌ እና የዩኒቨርቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ፊርማ ያረፈበት የሽልማት ምስክር ወረቀት በዩኒቨርሲቲ ደረጃ ማግኘቱን የሚታወስ ነው።
በድጋሜ እንኳን ደስ አለን!
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ህዳር 23/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
****************************************