የራያ ዩኒቨርሲቲ ስፖርት ልዑካን ቡድን አባላት በአዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በሚካሄደው የ2017 ዓ.ም የመንግስት ዩኒቨርሲቲዎች የተማሪዎች ስፖርት ፌስቲቫል መክፈቻ መርኃ ግብር በድምቀት ተሳትፈዋል።
በመክፈቻ መርኃ ግብሩ የተገኙት የዩኒቨርሲቲያችን ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ተገኝተው ለዩኒቨርሲቲው ስፖርት ቡድን አባላት በማበረታታት ስፖርተኞቹ በውድድራቸው በስፖርታዊ ጨዋነት ለውጤት እንዲጫወቱ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።
የስፖርት ፌስቲቫሉ ከጥር 17 እስከ 27/ 2017 ዓ.ም በአዲስ አበባ የሚካሄድ ሲሆን ራያ ዩኒቨርሲቲ በእግር ኳስ፣ አትሌቲክስ እና የባህል ስፖርት ተሳታፊ ይሆናል።