የራያ ዩኒቨርሲቲ የሕግ ትምህርት ቤት ከመኾኒ እና ራያ ዓዘቦ ማሕበራዊ ፍርድ ቤቶች ዘላቂ ትስስር ለመፍጠር ምክክር/ውይይት መድረክ አካሄደ።

የራያ ዩኒቨርሲቲ ህግ ትምህርት ቤት ከ USAID/OTI ESP ጋር በመተባበር የመኾኒ እና የራያ ዓዘቦ ማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ዘላቂ ትስስር ለመፍጠር ዛሬ ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ/ም በመኾኒ ከተማ ምክክር/ውይይት መድረክ አካሄደ።
በምክክር መድረኩ የተገኙት የትምህርት ቤቱ ዲን መምህር መሐመድ ባዩ ባደረጉት ንግግር ከማህበራዊ ፍርድ ቤቶቹ ዘላቂ ትስስር መፍጠር የሕግ የዓቅም ግንባታ ስራዎች ለማከናወን ያስችላል ሲሉ የምክክር መድረኩ ዓላማ በሰፊው አብራርተዋል።
የትምህርት ቤቱ የምርምር እና ማህበረሰብ አገልግሎት አስተባባሪ እና መምህር በርሀ ገሰሰው በማህበራዊ ፍርድ ቤቶች ዙርያ ጥናታዊ ፅሁፍ ያቀረቡ ሲሆን የምክክር መድረኩ ተሳታፊዎች በበኩላቸው በስራ ዘርፋቸው ያሉ መልካም ተሞክሮዎች፣ እያጋጠሙ ያሉ ችግሮችና የወሰዷቸው መፍትሔዎች በማጋራት ከትምህርት ቤቱ በቀጣይነት ትስስር መፍጠር ለስራቸው አጋዥ እንደሚሆን እና እንዲህ ዓይነት መድረኮችጨተጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው ሃሳባቸውን ሰጥተዋል።
*****************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ጥቅምት 09 ቀን 2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************************