የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ከሁለቱም ምክትል ፕረዚደንቶች በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (Key Performance Indicators) ስምምነት ተፈራርመዋል

በትምህርት ሚኒስቴር እና በራያ ዩኒቨርሲቲ መካከል በቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (Key Performance Indicators) ስምምነት ታኅሣሥ 16/2017 ዓ.ም  የተፈረመውን ስምምነት ተከትሎ የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ከዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማኅበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ እና የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ በዩኒቨርሲቲው ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (Key Performance Indicators) ዙርያ ታኅሣሥ 22/2017 ዓ.ም ስምምነት ተፈራርመዋል።

የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ በስምምነት ስነ ስርዓቱ እንደተናገሩት ዩኒቨርሲቲያችን ብቃትና ችሎታ ያላቸው ባለሙያዎች ለማፍራት እና ግልጽነት እና ተጠያቂነትን ለማስፈን  ባለን ጠንካራ ሰራተኛ ውጤታማ ስራዎችን እንሰራለን ብለዋል።

የዩኒቨርሲቲው የስትራቴጂክ ጉዳዮች ሥራ አስፈፃሚ አቶ ሃይለኪሮስ ከበደ በመማር ማስተማር፣ ምርምር፣ ፈጠራ እና ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ማህበረሰብ ጉድኝት እና አገልግሎት፣ ዓለም አቀፍ ትስስር እና ተሳትፎ እንዲሁም ዘርፈ ብዙ የአስተዳደር ስራዎች ትኩረቱን ያደረገ የዩኒቨርሲቲው ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች በዝርዝር አቅርበዋል፡፡

በቀረበው ዝርዝር የዩኒቨርሲቲ ቁልፍ የአፈጻጸም አመላካቾች (Key Performance Indicators) ዙርያ የዩኒቨርሲርሲቲው ካውንስል አባላት የተለያዩ ጥያቄዎች አንስተው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል፡፡

ስምምነቱ ሥራን ውጤት ተኮር ለማድረግና ሙያዊና ክህሎታዊ ልህቀት ለማዳበር እንዲሁም ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ለማካሄድ ወሳኝ ሚና ይኖረዋል፡፡


ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታኅሣሥ 23 /2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!

የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ

Facebook: https://www.facebook.com/RayaUniversityofficial

Website: https://www.rayu.edu.et/

************************************