የዩኒቨርሲቲውን ከፍታ ለማስቀጠል ከመምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ጋር ውይይት ተደረገ።

ዩኒቨርሲቲው በ2017 ዓ/ም የተቀናጀ ውጤታማ ስራ ለመስራት እና የዩኒቨርሲቲውን ከፍታ ለማስቀጠል ከዩኒቨርሲቲው መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ጋርዛሬ መስከረም 10/2017 ዓ/ም ውይይት ተደረገ።
በውይቱ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ባደረጉት ንግግር በ2016 ዓ/ም በአካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ማህበረሰብ ጉድኝት እና አስተዳደር ዘርፍ የተመዘገበ ከፍተኛ ውጤት በቀጣይ ዓመትም (2017 ዓ/ም) ተጠናክሮ ይቀጥላል በማለት በ2017 ዓ/ም በአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ማህበረሰብ ጉድኝት እና አስተዳደር ዘርፍ ሊሰሩ የሚገባቸው ቁልፍ እና ዓበይት ተግባራት ማብራርያ ሰጥተዋል።
በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞች እና የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን በ2017 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲው በየዘርፉ የሚገኙ የተለያዩ አካላት ተቀናጅተው ውጤታማ ስራዎች በመስራት የዩኒቨርሲቲውን ከፍታ ለማስቀጠል ነእንደሚተጉ ቃል ገብተዋል፡፡
**************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
መስከረም 10/2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************************