የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ነጥብ ላመጡ የጋርዮሽ ሳይንስ (Science Shared program) 12ኛ ክፍል ተማሪዎች ሽልማት እና ዕውቅና ተደረገላቸው።

ራያ ዩኒቨርሲቲ በጋርዮሽ ሳይንስ መርሃ ግብር (Science Shared Program) ከ2011 ዓ/ም ጀምሮ እያስተማራቸው ከነበሩ አሥራ አራት የ12ኛ ክፍል ተማሪዎች የ2016 ዓ/ም ሀገር አቀፍ የሁለተኛ ደረጃ መልቀቂያ እና የዩኒቨርሲቲ መግቢያ ፈተና ተፈትነው 13ቱም (92.86%) የማለፊያ ነጥብ ሲያገኙ፣ 1 ተማሪ ደግሞ የማካካሻ ትምህርት (Remedial) ዕድል ተጠቃሚ መሆናቸውን ተከትሎ የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ለተማሪዎቹ የዕውቅና እና ማበረታቻ መርሃ ግብር ዛሬ መስከረም 09/2017 ዓ/ም ተካሄደ።
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለተማሪዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ራያ ዩኒቨርሲቲ ጥራት ያለው ትምህርት እየሰጠ የሚገኝ ዩኒቨርሲቲ ነው ብለዋል።
ፕርፌሰር ታደሰ ለተማሪዎቹ ባስተላለፉት መልእክት ተማሪዎች በዩኒቨርሲቲ ቆይታችሁ ውጤታማ፣ ስራ ፈጣሪዎች ሆናችሁ ለህዝባችሁ እና ለሀገራችሁ ታማኝ አገልጋይ መሆን ይኖርባችኃል ብለዋል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ አባል እና የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ለተማሪዎቹ የእንኳን ደስ አላችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኃላ ራያ ዩኒቨርሲቲ እያስመዘገበ ላለው ከፍተኛ ውጤት ለሠራተኞቹ ሊመሠገኑ ይገባል ብለዋል።
በሥነ ስርዓቱ የኮሌጅ ዲኖች፣ ትምህርት ክፍል ሀላፊዎች፣ መምህራን፣ ተማሪዎች እና ሌሎች የሚመለከታቸው አካላት የተገኙ ሲሆን በመልቀቂያ ፈተናው ከፍተኛ ውጤት ላመጡ ሦስት ተማሪዎች የዕውቅና እና ገንዘብ ማበረታቻ ተበርክቷል።
*******************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
መስከረም 09/2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*********************************************

Loading