የራያ ዩኒቨርሲቲ አመራሮች፣ የሃይማኖች መሪዎች እና የሃገር ሽማግሌዎች፣ የአከባቢው ማኅበረሠብ ተወካዮች በጋራ በመሆን የ2017 ዓ.ም የልደት በዓልን ከዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች ጋር በድምቀት አክብረዋል።
ዩኒቨርሲቲው አሥተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ በምሳ መርኃ ግብሩ ተገኝተው ለተማሪዎቹ እንኳን አደረሳችሁ መልእክት ባስተላለፉበት ወቅት የገና በዓልን በይቅርታ እና በመተሳሰብ በማክበር የሰላም እና ዕርቅ ተምሳሌት ለመሆን የበኩላችሁን ሚና ማበርከት ይጠበቅባቹኃል ብለዋል።
የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መምህር ረዳኢ ስብሃቱ በዓሉን ምክንያት በማድረግ ባስተላለፉት መልእክት፤ የገና በዓል የአብሮነት እና የመደጋገፍ በዓል በመሆኑ ተማሪዎች በትምህርታችሁ ውጤታማ ለመሆን ጠንክራችሁ መማር ይኖርባቹኃል ብለዋል።
መጋቤ ኃዲሥ መምሕር ዕንቁባኅሪ ታመነ ለተማሪዎች ባስተላለፉት መልእክት፤ በዓሉ የሠላም፣ ፍቅር እና አንድነት እንዲሆን መልካም ምኞታቸውን ገልጸዋል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሠብ ጋር በመቀናጀት እየሰራ ያለው ውጤታማ ስራ በማድነቅ ይህን በዓል ስናከብር እርስ በርሳችን መከባበር እና መፋቀር አለብን ያሉት የሃይማኖት መሪው ሸኽ ሙሳ ናቸው።
የዩኒቨርሲቲው ተማሪዎች በበኩላቸው በተዘጋጀላቸው ልዩ የበዓል መርኃ ግብር መደሰታቸውን ገልፀዋል።
ዩኒቨርሲቲው በድጋሜ መልካም የልደት በዓል ይላል!
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታኅሣሥ 29/ 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሠባዊ ለውጥ!
የህዝብ እና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ