የፈተና ጥሪ ማስታወቂያ ለሠላምና ደኅንነት አገልግሎት ሥራ አሥፈጻሚ ተፈታኞች 

ራያ ዩኒቨርሲቲ ቀደም ሲል በቀን 26/02/2017 ዓ/ም ክፍት የሥራ ቦታ ካወጣው የኮንትራንት ቅጥር መካከል የሠላምና ደኅንነት አገልግሎት ሥራ አሥፈጻሚ ለመፈተን ተመልምላችሁ የነበራችሁ አመልካቾች ለቀን 16/04/2017 ዓ/ም ተብሎ የነበረ ፈተና በስራ ጫና ምክንያት ለሌላ ግዜ እንደ ተቀየረ እና በቀጣይ ጊዜ የምናሳውቅ መሆናችን ገልፀን እንደ ነበር ይታወቃል። በዚህ መሰረት ሐሙስ 01/05/2017 ዓ/ም ጧት 4:00 በራያ ዩኒቨርሲቲ ግቢ የብቃትና ሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አሥፈጻሚ ጽ/ቤት ማንነታችሁ የሚገልፅ መታወቂያ ይዛችሁ እንድትመጡ እንገልፃለን።

Loading