በሃገር አቀፍ ደረጃ ከጥር 26 – 30/ 2017 ዓ.ም የሚሰጠው መውጫ ፈተና (Exit Exam) ራያ ዩኒቨርሲቲ አስፈላጊውን ግብኣት በማሟላት እና በቂ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹን አጠናቅቆ ተፈታኞች እየተጠባበቀ ይገኛል።
ይህ የተሳካ እንዲሆን በዩኒቨርሲቲው የአካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት የሚመራ ግብረ ሃይል ተቋቁሞ በየጊዜው ክትትል ማድረጉን ተገልጿል።
የኮሚቴው ሰብሳቢ ዶ/ር ነጋ ዓፈራ የቅድመ ዝግጅት ስራዎቹ የተሳካ እንዲሆን አስተዋጽኦ ላበረከቱ አካላት ምስጋናቸውን በማቅረብ ፈተናውን እስኪጠናቀቅ ተገቢውን ድጋፍና ክትትል እንደሚደረግ ገልጸዋል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ጥር 25/ 2017 ዓ.ም ዕውቀት ለማኅበረሠባዊ ለውጥ! የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈጻሚ |