ዲጂታል፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የአገልግሎት አቅርቦት ስርዓት ለመዘርጋት የአሥተዳደር ሠራተኞቻችን ዕውቀት፣ ብቃት፣ ግብረ ገብነት እና ተነሳሽነት ማጠናከር ወሳኝ ነው፦ ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር)

አዲሱን የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 ለአሥተዳደር ሠራተኞች የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ዛሬ መጋቢት 04/ 2017 ዓ.ም በብቃትና ሰው ሃብት አሥተዳደር ሥራ አሥፈጻሚ ጽ/ቤት በዩኒቨርሲቲው ስማርት ክፍል ተሰጥቷል።
የአሥተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ ስልጠናው ተገኝተው ባስተላለፉት መልእክት አዲሱን የፌደራል መንግስት ሠራተኞች አዋጅ መሰረት የአሥተዳደር ሠራተኞቻችን ዕውቀት፣ ብቃት፣ ግብረ ገብነት እና ተነሳሽነት በማጠናከር በዩኒቨርሲቲው ዲጂታል፣ ቀልጣፋና ተደራሽ የአገልግሎት አቅርቦት ስርዓት እንዲኖር በትኩረት ይሰራል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው ብቃትና ሰው ሃብት አሥተዳደር ሥራ አሥፈጻሚ አቶ ካሕሳይ ፍቃዱ አዲሱን የፌደራል መንግስት ሰራተኞች አዋጅ ቁጥር 1353/2017 መሰረት በማድረግ የሰራተኞች ብቃትና ምዘና ስርዓት፣ የቅጥር፣ የደረጃ ዕድገት እና የዝውውር ዝርዝር ገለጻ አድርገዋል።
በዩኒቨርሲቲው የሰው ሃብት አሥተዳደር በድን መሪ አቶ ብርሃኑ ግርማይ በበኩላቸው አዲሱን መመሪያን ትኩረት አድርገው የሥራ ሰዓትና ፍቃድ፣ የሥራ አከባቢ ደህንነት እና ጤንነት፣ የዲሲፕሊን እርምጃዎች እና የቅሬታ አፈታት ሂደት እና የመንግሥት ሠራተኞች የሥራ ውል ማቋረጥ እና ማራዘም ጉዳዮች ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በመጨረሻም ከአሥተዳደር ሰራተኞር ጋር በተደረገ ውይይት የተለያዩ ሀሳብ አስተያየት እና ጥያቄዎች ተነስተው በሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እና ማብራሪያ ተሰጥቷል።
********//********************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ መጋቢት 04/ 2017 ዓ.ም
Knowledge for Societal Change!
Executive for Public and International Relations
********//********************************