የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ግዥ ኤጀንሲ ልኡካን ቡድን አባላት ከዩኒቨርስቲው ከፍተኛ አመራሮች ጋር ውይይት እና የመስክ ምልከታ አደረጉ።
**********
ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ ግዥ ኤጀንሲ የመጡ የልኡካን ቡድን አባላት ታህሳስ 19/2016 ዓ/ም ወደ ዩኒቨርሲቲው ሲገቡ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ እና የአስተዳደርና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ መልካም አቀባበል አድርገውላቸዋል።
የልኡካን ቡድኑ አባላት ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር ውይይት አድርገዋል። የውይይቱ ዋና ዓላማ ዩኒቨርሲቲው በተለያየ መንገድ ለማገዝ እና ለማበረታታት ነው።
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የዩኒቨርሲቲው አጠቃላይ እንቅስቃሴ እና በዩኒቨርሲቲው እያጋጠሙ ያሉት የተለያዩ እንቅፋቶች ለልኡካን ቡድኑ አባላት ገለፃ አድርገዋል።
በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ በበኩላቸው ዩኒቨርሰቲው ውጤታማ ስራ ለመስራት እያጋጠሙት ያሉት ችግሮች አቅርበዋል።
የልኡካን ቡድኑ አባላት ዩኒቨርሲቲውን ለማገዝ እና ለሚያጋጥሙት ችግሮች ሁነኛ መፍትሄ ለመስጠት እንዲሁም በተለያየ መንገድ ለማገዝ ቁርጠኛ መሆናቸውን በውይይቱ ተናግረዋል።
በመጨረሻም የልኡካን ቡድኑ አባላት ከዩኒቨርሲቲው አመራሮች ጋር በመሆን የተማሪዎች መኝታ ክፍል፣ መመገብያ አዳራሽ እና በዩኒቨርሲቲው አዲስ እየተሰሩ ያሉ ግንባታዎች እንዲሁም የተለያዩ የዩኒቨርሲቲው እንቅስቃሴዎች ጎብኝተዋል።
****
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ታህሳስ 19/2016 ዓ/ም
*****
English Version
Raya University
December 29, 2023
***
The Delegates of the FDRE Marketing and Procurement Agency Visited Raya University
********
The Delegates of the FDRE Marketing and Procurement Agency, led by Haji Ibsa, the Director of the Marketing and Procurement Agency, visited Raya University and discussed Raya University’s top managements on December 29/2023 at the President’s Office.
Prof. Tadese Dejenie, Raya University’s president, briefed them the overall damage of the University caused by the war of Tigrai, and the core problems of the University that hinder quality in education.
Of which, the absence of Nursery School, Staffs’ Residence, Absence of Vehicles, the presence of inadequate Dormitory and Classroom Buildings in relation to the high inflation unleashed in the country.
Ato Haji Ibsa, Director of the Ethiopian Marketing and Procurement Agency, on his part having realized the overall problems of the University, expressed his great commitment and willingness to make every possible effort to support the University.
Knowledge for Societal Change!
Executive for Public and International Relation
Facebook: https://www.facebook.com/Raya University/
Website: www.rayu.edu.et