በራያ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት ሲካሄድ የነበረው የ2016 ዓ/ም ጥምቀት ዋንጫ በደማቅ ስነ ስርዓት ተጠናቋል።

የ2016 ዓ/ም የጥምቀት በዓልን ምክንያት በማድረግ ከጥር 07-10/2016 ዓ/ም በራያ ዩኒቨርሲቲ አዘጋጅነት በአክሱም፣ ራያ፣ ዓዲ ግራት እና መቐለ ዩኒቨርሲቲዎች መካከል ሲካሄድ የነበረው ስፖርታዊ ውድድር በደማቅ ስነ ስርዓት ተጠናቋል።
በመረብ ኳስ በተደረገ የዋንጫ ጨዋታ መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለዓዲ ግራት ዩኒቨርሲቲ 3 ለ 0 በማሸነፍ የ2016 ዓ/ም የመረብ ኳስ ጥምቀት ዋንጫ አሸናፊ ሆኗል።
የ2016 ዓ/ም የእግር ኳስ ጥምቀት ዋንጫ ዓዲ ግራት ዩኒቨርሲቲ እና መቐለ ዩኒቨርሲቲ ባደረጉት ጨዋታ መደበኛ የጨዋታ ክፍለ ጊዜ ጥሩ ፉክክር የታየበት እና 1 አቻ የተጠናቀቀ ነበር። አሸናፊው ለመለየት በተሰጠ የፍፁም ቅጣት ምት (Penalty) ግን ዓዲ ግራት ለመቐለ ዩኒቨርሲቲ 5 ለ 4 በማሸነፍ ዋንጫ አንስቷል።
በመዝግያ ስነ ስርዓቱ የተገኙት የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) ለአሸናፊ ቡድኖች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ውድድሩ በዩኒቨርሲቲዎች መካከል ጠንካራ ወዳጅነት ለመፍጠር ትልቅ አስተዋፅኦ ስለሚያበረክት ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።
ራያ ዩኒቨርሲቲ በ2016 ዓ/ም ጥምቀት ዋንጫ ለተሳተፉ ዩኒቨርሲቲዎች የምስክር ወረቀት እንዲሁም በመረብ እና እግር ኳስ አንደኛ ለወጡ ቡድኖች የዋንጫ ሽልማት አዘጋጅቷል።
በመጨረሻም ቀጣይ ውድድሩ መቐለ ዩኒቨርሲቲ እንደሚያዘጋጅ ከውድድሩ ኮሚቴው ለማወቅ ተችሏል።
***************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ጥር 10/2016 ዓ/ም
*****************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
ድረ ገፅ: www.rayu.edu.et