የዩኒቨርሲቲው ግንባታዎች የደረሱበት ደረጃ ለዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል እና ከፍተኛ አመራሮች ሪፖርት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።

በዩኒቨርሲቲው እየተገነቡ ያሉ የተለያየ አገልግሎት የሚሰጡ ግንባታዎች እየተፋጠኑ መሆኖቸውን የሚታወቅ ሲሆን ግንባታዎቹ የደረሱበት ደረጃ ሪፖርት በኮንትራክተሮች ዛሬ የካቲት 07/2016 ዓ/ም ለዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል እና የደቡባዊ ትግራይ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቱ ኪሮስ እና ለዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች ቀርቧል።
ግንባታዎቹ በተያዘላቸው የጊዜ ገደብ እንዲጠናቀቁ በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ካሳሁን ጎፌ የሚመራ የሥራ አመራር ቦርድ አባላት ከዚህ በፊት ያስቀመጡት አቅጣጫ ለመገምገም በአቶ ሃፍቱ ኪሮስ የተመራ ውይይት ተካሂዷል።
በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር)፣ የአስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር) እንዲሁም ኮንትራክተሮች እና የፕሮጀክት አስተባባሪዎች ተሳትፈዋል።
በመጨረሻም በውይይቱ ለተነሱት የተለያዩ ጥያቄዎች በሚመለከታቸው የሥራ ሀላፊዎች ምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቷል።
****************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
👇👇👇
Facebook: https://www.facebook.com/Raya University