እንኳን ደስ አለን! ራያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኝ ተማሪዎቹን በከፍተኛ ውጤት አሳልፏል፡፡

በሀገር አቀፍ ደረጃ ከየካቲት 07-11/2016 ዓ/ም ለ2016 ዓ.ም ተመራቂ ተማሪዎች የተሰጠ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ራያ ዩኒቨርሲቲ 96.47% ተማሪዎች አሳልፏል፡፡
በራያ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ለመፈተን የሚያስችል የተሟላ የአይ ሲ ቲ መሰረተ ልማት ባለመኖሩ ተማሪዎቻችን በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እንዲፈተኑ ተደርጓል፡፡
ይህ ውጤት እንዲመዘገብ ትልቅ አስተዋፅኦ ላበረከቱ መምህራን፣ የዩኒቨርሲቲው አመራሮች እና ሥራ አመራር ቦርድ ምስጋና ይገባቸዋል፡፡
ተማሪዎች እና የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ እንኳን ደስ አላችሁ!
***************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
***************