የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት መጋቢት 19/2016 ዓ/ም ባደረጉት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ በሰጡት አቅጣጫ መሰረት ግምገማ ተካሄደ፡፡

የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባላት መጋቢት 19/2016 ዓ/ም ባደረጉት 5ኛ መደበኛ ስብሰባ በዩኒቨርሲቲው በታህሳስ ወር 2016 ዓ/ም የተጀመረው የከብትና በግ ማድለብ እንዲሁም የአትክልትና ፍራፍሬ እርባታ ፕሮጀክቶች በተለያዩ የቴክኒካል እና አመራር ክፍተቶች ምክንያት በሚጠበቀው መልኩ ውጤታማ አለመሆናቸውን ገምግመው የመፍትሄ ሀሳብ አስቀምጠዋል፡፡
በተመሳሳይ መልኩ በዩኒቨርሲቲው ከሚመለከታቸው ሀላፊዎችና ባለሙያዎች ጋር የተጀመሩ የፕሮጀክት ስራዎች ለማጠናከር መጋቢት 23 እና 25/2016 ዓ/ም ውይይት የተደረገ ሲሆን በውይይቱ ችግሮቹን ለመፍታት የመፍትሄ ሀሳብ ተቀምጧል፡፡ በተጨማሪም በውይይቱ ሁሉም የበኩሉን አስተዋፅኦ በማድረግ ውጤታማ መሆን እንደሚያስፈልግ ስምምነት ላይ ተደርሷል::
በውይይቱ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ እንደገለፁት የዩኒቨርሲቲያችን የትኩረት መስክ (Focus Area) ግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ስለሆነ ውጤታማ የምርምር ውጤቶች ላይ በመሰማራት ማህበረሰቡን ማገልገል ይገባናል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ክብሮም ካሕሱ በበኩላቸው የጀመርናቸው የግብርና እና ተፈጥሮ ሀብት ልማት ስራዎቻችን ከሚመለከታቸው ሀላፊዎች እና ባለሙያዎች ጋር በቅንጅት አጠናክረን በመስራት የውስጥ ዓቅማችን እና ገቢያችን ማሳደግ አለብን ብለዋል።
ዶ/ር ክብሮም አክለው እንደገለፁት ባለን ውሱን በጀት ለቀጣይ የዶሮ፣ ንብ፣ ማንጎ እና አፕል እርባታ ስራዎች ላይ ትኩረት ሰጥተን መስራት አለብን ብለዋል፡፡
በመጨረሻም በውይይቱ ከባለሙያዎች ለተነሱ ሀሳቦች እና ጥያቄዎች በሚለከታቸው አካላት ማብራርያ ተሰጥቷል፡፡
*********************************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*********************************