የዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ/ም የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ለዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ቀረበ።

በዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) የቀረበ የዩኒቨርሲቲው የ2016 ዓ/ም የዘጠኝ ወራት ሥራ አፈፃፀም ሪፖርት የዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ጋር በዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ክሊኒክ አዳራሽ ሚያዝያ 01/2016 ዓ/ም በጥልቀት ተወያይተዋል።
ዩኒቨርሲቲው በ2016 ዓ/ም 9 ወራት በአካዳሚክ፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ማህበረሰብ አገልግሎት፣ አስተዳደር ጉዳዮች፣ የተለያዩ ግንባታዎች፣ መሰረተ ልማት እና ግቢ ውበት ዘርፍ ያከናወናቸው አንኳር ሥራዎች በፕረዚደንቱ የቀረቡ ሲሆን ዩኒቨርሲቲው በ2015 ዓ/ም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ትምህርት ሚኒስቴር በትግራይ ክልል ባሉ የመንግስት ትምህርት ተቋማት ዳግም ትምህርት ለማስጀመር ባዘጋጀው እቅድ መሰረት ዩኒቨርሲቲው ከሰኔ እስከ ሰኔ በሚል የ13 ወራት የማካካሻ ትምህርት አዘጋጅቶ ተማሪዎቹን አብቅቶ ማስመረቁ፣ የዩኒቨርሲቲ መውጫ ፈተና (Exit Exam) 96.05% ተማሪዎችን በማሳለፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ደረጃ መያዙን፣ በድህረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) እና በከፍተኛ ትምህርት መረጃ አስተዳደር ስርዓት (HEIMS) አመርቂ ውጤት መመዝገቡ፣ ከከንሳስ ስቴት ዩኒቨርሲቲ (USA) የተገኘው የ$ 100,000 ፕሮጀክት፣ የእንስሳት ማድለብ ሥራዎች፣ ከማገዶ ወደ ኤሌክትሪክ የተቀየረ የተማሪዎች ምግብ ማብሰያ ሙሉ በሙሉ ተግባራዊ መሆኑ፣ ለማህበረሰብ በርካታ የሥራ እድሎችን የፈጠሩ ግንባታዎች እና ሌሎች የመሰረተ ልማት ሥራዎች፣ የነዳጅ ማደያ ግንባታ፣ ፅዱና አረንጓዴ ግቢ ውበት ለመፍጠር እየተሰሩ ያሉ ሥራዎች እንዲሁም ተግባራዊ የተደረገ የሰራተኞች የስራ ድልድል በዝርዝር ቀርበዋል።
በውይይቱ ዩኒቨርሲቲው በቀጣይ ከዚህ በበለጠ ውጤታማ ለማድረግ ስራዎችን ዲጂታላይዝድ ማድረግ እና በሥራ አፈፃፀም ውል መሰረት ተጠያቂነት እና ግልፅነት በማስፈን የታዩ ድክመቶች ለማሻሻል በቅንጅት መስራት እንደሚያስፈልግ ተገልጿል። በተያያዘ መልኩ ከዩኒቨርሲቲው ካውንስል አባላት ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በዩኒቨርሲቲው አካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ ምክትል ፕረዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) እና የአሰተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር) ምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቷል።
በመጨረሻም የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ከሁለቱም ምክትል ፕረዚደንቶች ጋር የ2016 ዓ/ም 4ኛ ሩብ ዓመት ሥራ አፈፃፀም ውል ተፈራርመዋል። በቀጣይ ደግሞ ሁለቱም ምክትል ፕረዚደንቶች በስራቸው ከሚገኙ ሁሉንም የሥራ ዘርፎች የሥራ አፈፃፀም ውል የሚፈራረሙ ይሆናል።
**********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሚያዝያ 01/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
**********************

Loading