በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የ2016 ዓ/ም የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በደማቅ ስነ ስርዓት ተጠናቋል።

በራያ ዩኒቨርሲቲ ከየካቲት 09/2016 ዓ/ም ጀምሮ በኮሌጆች መካከል በየሳምንቱ በታላቅ ፉክክር ሲካሄድ የነበረው የተማሪዎች ዓመታዊ የስፖርት ውድድር በእግር ኳስ ውድድር የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ፣ በመረብ ኳስ ደግሞ የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ አሸናፊነት ሚያዚያ 20/2016 ዓ/ም ፍጻሜውን አግኝቷል።
በተደረገ የእግር ኳስ የፍጻሜ ጨዋታ የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ ለረመዲያል ተማሪዎች (Remedial Students) 2 ለ 1 በሆነ ውጤት አሸንፈው ዋንጫውን አንስተዋል፡፡ በመረብ ኳስ ደግሞ የተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ ተማሪዎች ለህግ ትምህርት ቤት ተማሪዎች 2 ለ 0 በሆነ ውጤት አሸንፈው የአንደኝነት ደረጃን በመያዝ ውድድራቸውን በማጠናቀቅ የዋንጫ ሽልማታቸውን ከዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መ/ር ረዳኢ ስብሃቱ ተረክበዋል፡፡
በእግር ኳስ ውድድር ከፍተኛ ጎል አግቢ ተማሪ ገ/መስቀል መሓሪ ከማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ፣ ኮከብ ተጫዋች ተማሪ ደቦል ጂን ከረመዲያል (Remedial) እና ኮከብ ግብ ጠባቂ ተማሪ ጀማል ሽኩር ከ ረመዲያል (Remedial) ሽልማታቸውን ከእለቱ የክብር እንግዳና የማህበራዊ ሳይንስና ስነ ሰብ ኮሌጅ ዲን መ/ር ግርማይ ግደይ ተረክበዋል።
በሽልማት ስነ ስርዓቱ የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች አገልግሎት ዲን መ/ር ረዳኢ ስብሃቱ ባስተላለፉት መልእክት ለአሸናፊዎቹ እንኳን ደስ አላችሁ አላችሁ በማለት ተማሪዎች በውድድሩ ላሳዩት ፍጹም ስፖርታዊ ጨዋነት የሚመሰገን እና ተጠናክሮ መቀጠል ያለበት ነው ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው የተማሪዎች ስብዕና ግንባታ ምክትል ዲን መ/ር መንግስቱ ጠዓመ በበኩላቸው ይህንን ውድድር በተሳካ ሁኔታ እንዲካሄድ ዩኒቨርሲቲው ያደረገላቸው ድጋፍ ለቀጣይ ከዚህ የበለጠ እንድንሰራ ስለሚያደርግ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል፡፡ መ/ር መንግስቱ አክለው ለአሸናፊ ተማሪዎች እንኳን ደስ አላችሁ በማለት ተማሪዎች በውድድሩ ላሳያችሁት የስፖርት ፍቅር፣ መተሳሰብ እና የአብሮነት መንፈስ በማድነቅ ይህን ውድድር የተሳካ እንዲሆን ትልቅ አስተዋጽኦ ላበረከቱ የስፖርት ባለሙያዎች በዩኒቨርሲቲው ስም አመስግነዋል፡፡
ተሳታፊ ተማሪዎች በበኩላቸው ዩኒቨርሲቲው ባዘጋጀላቸው የስፖርት ውድድር መርሃ ግብር በጣም ደስተኞች መሆናቸውን ገልጸዋል።
**********************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሚያዝያ 21/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አሥፈፃሚ
ለበለጠ መረጃ
**********************