ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው በዝውውር እና ቅጥር ለመጡ መምህራን ስልጠና ተሰጠ።

ዩኒቨርሲቲዎች ብቃት ያላቸው እና የሰለጠኑ የሰው ሀይል እንዲያፈሩ የመምህራን ዲሲፕሊን ወሳኝ ስለሆነ በራያ ዩኒቨርሲቲ የስነ ምግባርና መከታተያ ሥራ አስፈፃሚ የተዘጋጀ የአካዳሚክ ሰራተኞች መብት ማስከበርያ፣ የዲሲፕሊን ጥፋት እና ቅጣት አወሳሰን ሥነ ስርዓት የሚደነግግ የዲሲፕሊን ኮድ እና የትምህርት ሙስና (Academic Corruption) ጉዳዮች ስልጠና ከ2016 ዓ/ም ጀምሮ ወደ ዩኒቨርሲቲው በዝውውር እና ቅጥር ለመጡ መምህራን ዛሬ ግንቦት 17/2016 ዓ/ም ተሰጠ።
በስልጠናው የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ዶ/ር ነጋ ዓፈራ (የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ ምክ/ፕረዚደንት) የሰለጠነ የሰው ኃይል ለማፍራት፣ ችግር ፈቺ ጥናትና ምርምር ለማካሄድና ሕብረተሰቡን ለማገልገል የመምህራን ሚና ወሳኝ ስለሆነ እያንዳንዱ መምህር የሥራ ድርሻውን በስርዓት መከወን፣ መብትና ግዴታውን በፍጹም የባለቤትነት ስሜትና መልካም ስነ-ምግባር መተግበር፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት ማስፈን ይጠበቅበታል ብለዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የህግ ትምህርት ክፍል ሀላፊ እና መምህር በረከት አስመላሽ የአካዳሚክ ሰራተኞች መብት ማስከበርያ፣ የዲሲፕሊን ጥፋት እና ቅጣት አወሳሰን ሥነ ስርዓት የሚደነግግ የዲስፕሊን ኮድ ዓላማና እና ጠቅላላ ድንጋጌዎች፣ የተከለከሉና ጥፋተኛ የሚያሰኙ ድርጊቶች፣ የክርክር አቀራረብ ሥነ ሥርዓት፣ የአካደሚክ ሠራተኞች ዲስፕሊን ኮሚቴ፣ የቅጣት አወሳሰን፣ የቅሬታ አቀራረብ ሥነ-ሥርዓት እንዲሁም ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች ትኩረት ያደረገ ስልጠና ሰጥተዋል፡፡
በዩኒቨርሲቲው የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ የስነ ዜጋ እና ስነ ምግባር ትምህርት ክፍል መምህር ግርማይ ሃ/ኪሮስ የትምህርት ሙስና (Academic Corruption) ምንነት፣ መንስኤዎች፣ ባህርያት፣ ዓይነቶች፣ ውጤቶች እና መከላከያ ዘዴዎች ማብራርያ ሰጥተዋል።
ተሳታፊ መምህራን በበኩላቸው የተለያዩ ሀሳቦች፣ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች አንስተው የዩኒቨርሲቲው የአካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ ምክትል ፕረዚደንት ልዩ ረዳት ዶ/ር መሐመድአወል የሱፍ፣ የስነ ምግባርና መከታተያ ሥራ አስፈፃሚ ወ/ሮ ካሕሱ ቦለድ እና ሌሎች ሚመለከታቸው አካላት ምላሽ እና ማብራርያ በመስጠት ስልጠናው ተጠናቋል።
***********************
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
******************
ለበለጠ መረጃ👇👇👇ይመልከቱ።