ራያ ዩኒቨርሲቲ እና ማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ከ2008 ዓ/ም ጀምረው በኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ተማሪዎች ለማብቃት በትብብር እየሰሩ መምጣታቸው የሚታወስ ሲሆን ይህን ግንኙነት ለማጠናከር የራያ ዩኒቨርሲቲ ኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ እና የማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ግንቦት 25/2016 ዓ/ም የጋራ ውይይት አድርገዋል።
የውይይቱ ዋና ዓላማ ሁለቱም ተቋማት ብቁ ተማሪ ለማፍራት ውይይት ለመያየት እና ቀጣይ አቅጣጫዎችን ለማስቀመጥ ነው።
የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) የመክፈቻ ንግግር ያደረጉ ሲሆን በራያ ዩኒቨርሲቲ እና ማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ ያለውን ግንኙነት ለማጠናከር በርትተን እንሰራለን ብለዋል።
በራያ ዩኒቨርሲቲ የኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን መ/ር ተስፋይ አብርሃ (ረዳት ፕሮፌሰር) የራያ ዩኒቨርሲቲ እና ማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅ የጋራ መስሪያ ዕቅድ መግቢያ፣ ዓላማ፣ ጠቀሜታ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና መፍትሔዎቻቸው በዝርዝር ገለፃ አድርገዋል።
በውይይቱ ከሁለቱም ተቋማት ለተነሱ ሀሳብ፣ አስተያየት እና ጥያቄ በዩኒቨርሲቲው አካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገ/ ምክትል ፕረዚደንት ልዩ ረዳት ዶ/ር መሓመድአወል የሱፍ፣ የራዩ ኢንጅነሪንግ እና ቴክኖሎጂ ኮሌጅ ዲን መ/ር ተስፋይ አብርሃ እና የማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮለረጅ ዲን መ/ር ግርማይ ሓጎስ የማይጨው ፖሊ ቴክኒክ ኮሌጅምላሽ እና ማብራርያ ተሰጥቷል።
*****************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ግንቦት 25/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************
ለበለጠ መረጃይመልከቱ።
Website: https://www.rayu.edu.et/