ራያ ዩኒቨርሲቲ ከተለያዩ ትምህርት ቤቶች ለመጡ የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች ልዩ የማጠናከርያ ትምህርት (Tutorial) ግንቦት 22/2016 ዓ/ም በይፋ መጀመሩን የሚታወስ ሲሆን ዛሬ ግንቦት 24/2016 ዓ/ም ደግሞ የትግራይ ክልል፣ የደቡባዊ ትግራይ ዞን እና የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች እንዲሁም የአከባቢው ማህበረሰብ እና የሀይማኖች መሪዎች በጋራ በመሆን በማይጨው ከተማ የህዝብ መሰብሰብያ አዳራሽ የእንኳን ደህና መጣችሁ መርሀ ግብር አዘጋጁ።
በስነ ስርዓቱ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ ለተማሪዎቹ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን በብቃት ለማስተማር ዝግጁ ስለሆነ እናንተም በዩኒቨርሲቲው ቆይታችሁ በርትታችሁ በማጥናት በዕውቀት፣ ክህሎት እና ስነ ምግባር ውጤታማ መሆን አለባችሁ ብለዋል።
የትግራይ ክልል ትምህርት ቢሮ ምክትል ሀላፊ አቶ ረዳኢ ገ/ሄር በበኩላቸው ጥቅምት 2016 ዓ/ም ራያ ዩኒቨርሲቲ ለተቀበላቸው የ12ኛ ክፍል ተፈታኝ ተማሪዎች በሰጠው ልዩ የማጠናከርያ ትምህርት በጥሩ ውጤት እንዲያልፉ ማድረጉን የሚታወስ ሲሆን እናንተም በዩኒቨርሲቲው መመደባችሁ እንኳን ደስ አላችሁ ብለዋል።
አቶ ረዳኢ ገ/ሄር በንግግራቸው በትግራይ በነበረው ጦርነት የወደመውን የትግራይ ትምህርት የስነ ልቦና፣ ማህበራዊ እና ቁጠባዊ ፈተናዎች መፍትሄ ለማድረግ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር በትብብር እየሰራን እንገኛለን በማለት ለተማሪዎች ድጋፍ ላደረጉ አካላት አመስግነዋል።
የደቡብ ትግራይ ዋና አስተዳዳሪ እና የዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አባል አቶ ሃፍቱ ኪሮስ ለተማሪዎቹ እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተማሪዎች ጠንክራችሁ በመስራት ውጤታማ መሆን አለባችሁ ብለዋል።
በመጨረሻም የአባቢው ማህበረሰብ፣ ሃይማኖት መሪዎች እና የተለያዩ አመራሮች ተወካዮች ለተማሪዎቹ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልእክት ካስተላለፉ በኃላ ለእያንዳንዱ ተማሪ 2,000 ብር እና 4 ደብተር እና እስክርቢቶ ድጋፍ ተደርጓል።
*****************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ግንቦት 24/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና አለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************
ለበለጠ መረጃይመልከቱ።
Website: https://www.rayu.edu.et/