በዩኒቨርሲቲው የS.R.E ዲጂታል ቤተ መፃህፍት እና መረጃ አስተዳደር (Library and Documentation) መሽን ቴክኖሎጂ በመተግበር ተማሪዎች ለማብቃት እየተሰራ ነው።

ራያ ዩኒቨርሲቲ በቴክኖሎጂ ለማዘመን እና የተማሪዎች ብቃት ለማሻሻል እየተሰሩ ካሉ ስራዎች መካከል ዲጂታል የቤተ መፃህፍት እና መረጃ አስተዳደር ለተማሪዎች እና መምህራን ምቹ እና ፈጣን አገልግሎት የሚሰጥ የሲስተም ማሻሻያ የተደረገለት የS.R.E Digital Library Ultimate Version ተገጥሞ አገልግሎት የሚሰጥ ሲስተም በዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) የተመራ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራር አባላት ዛሬ ግንቦት 23/2016 ዓ/ም ጉብኝት አድርገዋል።
እንደ ባለሙያዎቹ ገለፃ የS.R.E Digital Library Ultimate Version አገልግሎት ተጠቃሚዎች የሚፈልጉት ኮሌጅ፣ ትምህርት ክፍል፣ መጽሃፍት፣ የትምህርት ዓይነት እና ምዕራፍ በቀላሉ በመፈለግ ማንበብ፣ ማውረድ፣ ወደ ሲስተሙ መጨመር ያስችላል።
የቤተ መፃህፍት እና መረጃ አስተዳደር (Library and Documentation) ሥራ አስፈፃሚ መ/ር መለሰ ካልኣዩ እንደገለፁት ስምንት ቴራ ባይት (8 TB) መያዝ አቅም (Storage) ያለው የዲጂታል ቤተ መፃህፍት አገልግሎት ያለ ኢንተርኔት ሞባይል ወይም ኮምፒውተር በመጠቀም በቀላሉ መጽሃፍትን ማንበብ እና ማውረድ እንዲሁም በፈተና ወቅት የቤተ መፃህፍት አገልግሎት መጨናነቅን ለመቀነስ ከቤተ መፃህፍት ውጭ እስከ 1.5 ኪሎ ሜትር ሬድየስ የሚሸፍን በተማሪዎች መኝታ ህንፃዎች አከባቢ እና በኮምፒዩተር ክፍሎች በሶፍትኮፒ መጽሃፍትን ለማንበብ ይረዳል ብለዋል::
ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ እንደገለፁት በሀገራችን 15 ተቋማት ብቻ የሚጠቀሙት የS.R.E Digital Library System ራያ ዩኒቨርሲቲ ተማሪዎቹን ብቁ ለማድረግ እና ዩኒቨርሲቲው ለማዘመን በትግራይ ክልል ብቸኛ የዲጂታል ቤተ መፃህፍቱ አገልግሎቱ ተጠቃሚ ነው ብለዋል።
በጉብኝት ሂደቱ የተገኙት የዩኒቨርሲቲው አካ/ምር/ቴክ/ሽግ/ማህ/አገልግሎት ምክ/ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ በበኩላቸው መምህራን እና የቤተ መፃህፍት እና ዲጂታል ሰራተኞች በአንድ ጊዜ ከ100 በላይ የሶፍትኮፒ መጽሃፍት፣ ቪዲዮ እና ድምጽ መማሪያዎችን እና ያላቸውን ሌሎች አጋዥ መጽሃፍት እና ጠቃሚ የትምህርት መረጃዎችን በዲጅታል ቤተ መፃህፍት መሽን ሲስተም አካውንት ተጠቅመው ማጋራት እንደሚችሉ አብራርተዋል።
*****************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ግንቦት 23/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************
ለበለጠ መረጃ👇👇👇ይመልከቱ።