የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የአረንጓዴ ዓሻራ ችግኝ ተከላ መርሃ ግብር በማይጨው ከተማ አካሄዱ።

በዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ፕሮፌሰር ታደሰ ደጀኔ የተመራ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ መምህራን እና አስተዳደር ሰራተኞች ለችግኝ ተከላ የተዘጋጀ ቦታ በማይጨው ከተማ 03 ቀበሌ ጎሎ ፓርክ ዛሬ ጧት ሐምሌ 04/2016 ዓ/ም ዩኒቨርሲቲው የከተማው ማህበረሰብ አካል መሆኑን ያረጋገጠበት እና የአከባቢው ማህበረሰብ በማነቃቃት ለችግኞቹ ተገቢውን እንክብካቤ እንዲደረግ የችግኝ ተከላ መርሃ ግብር አካሄዱ።
በችግኝ ተከላ መርሃ ግብሩ የደቡብ ትግራይ ዋና አስተዳዳሪ አቶ ሃፍቱ ኪሮስን ጨምሮ የዞኑ ከፍተኛ እና መካከለኛ አመራሮች፣ የከተማዋን ነዋሪዎች፣ የመንግስት እና መንግስታዊ ያልሆኑ መስሪያ ቤት ሰራተኞች እና ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።
ዩኒቨርሲቲው የአረንጓዴ ልማት መርሃ ግብር ለማሳካት በ2016 ዓ/ም ለሌሎች ተቋማት አርአያ የሆኑ የተለያዩ ውጤታማ ስራዎች እየሰራ መጥቷል።
በተገኘው መረጃ መሰረት በ2016 ዓ/ም ክረምት በዞኑ 6.2 ሚሊየን በከተማዋ ደግሞ ከ75,000 በላይ የሚበሉ አትክልት እና ፍራፍሬ እንዲሁም የተለያዩ ጠቀሜታ ያላቸው ችግኞች ለመትከል እቅድ ተይዟል።
*******************
ራያ ዩኒቨርሲቲ
ሐምሌ 04/2016 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
************************************