በራያ ዩኒቨርሲቲ የ2017 ዓ/ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት (DOCO) ተጀመረ።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ነባር መደበኛ የቅድመ ምረቃ ተማሪዎቹን ከመስከረም 13-14/2017 ዓ/ም ተቀብሎ የዩኒቨርሲቲው ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) እና የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ ምርምር ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ ጉድኝት ምክትል ፕረዚደንት ነጋ ዓፈራ (ዶ/ር) በተገኙበት ዛሬ መስከረም 15/2017 ዓ/ም መደበኛ የመማር ማስተማር ሂደት ጀምሯል።
መምህራን በተመደቡበት ክፍል በሰዓታቸው ተገኝተው መደበኛ የመማር ማስተማር ስራቸውን ጀምረዋል።
የዩኒቨርሲቲው መምህራን እና ተማሪዎች እንዲሁም አመራሮች ይእንዲሳካ ላደረጉት ውጤታማ ቅንጅት ዩኒቨርሲቲው ምስጋናውን ለማቅረብ ይወዳል።
************************************
ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ መስከረም 15/2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
************************************