የኢትዮጵያ ሚቲዎሮሎጂ ኢንስቲትዩት ትንበያ እንደሚያመለክተው በአሁኑ ወቅት በአብዛኞቹ የክልሉ አካባቢዎች ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ እንደሚኖር በጠቆመው መሰረት ወቅቱን ያልጠበቀ ዝናብ በደረሱ የአርሶ አደር ሰብሎች ላይ ጉዳት ከማድረሱ በፊት የራያ ዩኒቨርሲቲ የማህበረሰብ አገልግሎት ዳይሬክቶሬት የአጨዳ መርሃ ግብር አዘጋጅቶ የዩኒቨርሲቲው ከፍተኛ አመራሮች፣ መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞችና ተማሪዎች ዛሬ ሐሙስ ጥቅምት 28 /2017 ዓ/ም የአከባቢው አርሶ አደር የደረሱ ሰብሎችን በማጨድና በመሰበሰብ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ ውሏል።
የራያ ዩኒቨርሲቲ ፕረዚደንት ታደሰ ደጀኔ (ፕሮፌሰር) ዩኒቨርሲቲው ድጋፍ የሚያስፈልጋቸውን አርሶ አደሮች የደረሱ ሰብሎቻቸውን በማጨድ እና በመሰብሰብ የህዝቡ አጋር መሆኑን በተግባር አሳይቷል ብለዋል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር) በበኩላቸው የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የአርሶ አደሩን የደረሱ ሰብሎች የማጨድና የመሰብሰብ ስራ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ተናግረዋል።
********************************************
ዩኒቨርሲቲ ራያ ፤ ጥቅምቲ 28/ 2017 ዓ.ም
ፍልጠት ንማሕበረሰባዊ ለውጢ!
ፈፃሚ ስራሕ ርክብ ህዝብን ዓለም ለኻዊ ርክባትን
********************************************