በራያ ዩኒቨርሲቲ 25ኛው ዓለም አቀፍ የጂ አይ ኤስ ቀን (Intrenational GIS Day) በድምቀት ተከበረ

25 ኛው ዓለም አቀፍ የጂ አይ ኤስ ቀን ( 25th International GIS Day) በማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ የጂኦግራፊ እና አከባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል የተዘጋጀ መርሀ ግብር ዛሬ ህዳር 27/ 2017 ዓ.ም በድምቀት ተከብሯል።
የበዓሉ ቁልፍ ዓላማ የጂ አይ ኤስ (GIS) እና Remote Sensing (RS) ግንዛቤ ለመፍጠር፣ የጂ አይ ኤስ መተግበሪያዎች (GIS Applications) ለማስተዋወቅ እንዲሁም ሙያዊ ትስስር ለማጠናከር ነው።
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንትን በመወከል መምህር ህንፃ ገ/ገርግስ (ረዳት ፕሮፌሰር) ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር፤ ጂ አይ ኤስ (GIS) ለአንድ ሀገር እድገት ፈርጀ ብዙ ጠቀሜታ ያለው እና ጂ አይ ኤስ (GIS) በሰለጠነ ዘመን ቁልፍ የለውጥ መሳሪያ ነው ብለዋል።
የማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ ዲን መምህር ግርማይ ግደይ፤ ዓለም አቀፍ የጂ አይ ኤስ ቀንን (International GIS Day) በተመለከተ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን የጂ አይ ኤስ (GIS) ዓላማ፣ ጠቀሜታ እና መተግበሪያውች እንዲሁም በጂ አይ ኤስ(GIS) ዙርያ የሚታዩ የተዛባ እይታዎች፣ ተግዳሮቶች እና መልካም ዕድሎች ዝርዝር ሙያዊ ማብራሪያ ሰጥተዋል።
በተፈጥሮ እና ቀመር ሳይንስ ኮሌጅ የፊዚክስ ትምህርት ክፍል መምህር የሆኑት ገ/መድህን ጎዲፍ (ዶ/ር) “Delineation of Groundwater Potential Zones Using Remotely Sensed Data and GIS-Based Analytical Hierarchy Process (Insights from the Geba River Basin.” በተመለከተ ጥናታዊ ፅሁፍ አቅርበዋል።
በማህበራዊ ሳይንስ እና ስነ ሰብ ኮሌጅ የጂኦግራፊ እና አከባቢ ጥናት ትምህርት ክፍል መምህር እና ተመራማሪ ኪሮስ ፀጋይ (ረዳት ፕሮፌሰር) በበኩላቸው “Modeling Eragrostis “Teff” and Hordeum Vulgare L Cropland in Response to Food Insecurity in the Central Region of Ethiopia.” በተመለከተ ከጂ አይ ኤስ (GIS) ጋር በማያያዝ ጥናታዊ ፅሁፋቸውን አቅርበዋል።
የ ጂ አይ ኤስ (GIS) መተግበሪያ መሰረት በማድረግ “Improving Accuracy of Land Use Land Cover Classification Using Object-Based Fuzzy Approach In Suluh River Basin.” በእጩ ዶ/ር ሃይላይ ሓጎስ ቀርቧል።
በቀረቡ ጥናታዊ ፅሁፎች ዙርያ ከተሳታፊዎች ለተነሱ አስተያየቶች እና ጥያቄዎች በሚመለከታቸው አካላት ሙያዊ ማብራሪያ እና ምላሽ የተሰጠ ሲሆን ጥናታዊ ፅሁፋቸውን ያቀረቡ መምህራን የእውቅና ምስክር ወረቀታቸውን ከመምህርት አስመረት ኪዳኔ ተቀብለዋል።
በመጨረሻም የራያ ዩኒቨርሲቲ ኢንደስትሪ ትስስር ዳይሬክተር መምህርት አስመረት ኪዳኔ ባደረጉት የመዝጊያ ንግግር ጂ አይ ኤስ (GIS) እና Remote Sensing (RS) ለጥናትና ምርምር፣ መማር ማስተማር፣ ደጂታላይዜሽን እና እድገትና ለውጥ ወሳኝ ስለሆነ ተጠናክሮ መቀጠል አለበት ብለዋል።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ህዳር 27 /2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
*****************************************