በጭብጥ የምርምር መርኆች (Thematic Research Principles) ዙሪያ የዓቅም ግንባታ ለመምህራን ስልጠና ተሰጠ

የራያ ዩኒቨርሲቲ የምርምር፣ ህትመት፣ ስነ-ምግባር እና ኢንዳክሽን ዳይሬክቶሬት ያዘጋጀው የጭብጥ የምርምር መርኆች (Thematic Research Principles) የዓቅም ግንባታ ስልጠና ለመምህራን ዛሬ ሀሙስ ታህሳስ 03/ 2017 ዓ/ም ተሰጥቷል፡፡
የስልጠናው ዓላማ መምህራን የምርምር መርህ ተከትለው ወቅታዊ፣ ውጤታማ እና የተሟላ ምርምር በመስራት አስፈላጊውን ሪፖርት በግልፅነት እና ታማኝነት ለሚለከተው አካል እንዲያስረክቡ ለማስቻል ነው፡፡
የጭብጥ የምርምር መርኆች (Thematic Research Principles) በተመለከተ በእለቱ ጽሁፍ ያቀረቡት የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ልዩ ረዳት ዶ/ር መሐመድአወል የሱፍ ሲሆኑ ሀገራዊ እና የዩኒቨርሲቲው የጭብጥ የምርምር መርኆች (Thematic Research Principles) ገለፃ በማድረግ የሚሰሩ የምርምር ሥራዎች ችግሮችን የሚፈቱ እና አዲስ ዕውቀት ሊያስገኙ መሆን እንዳለባቸው አብራርተዋል፡፡
የዩኒቨርሲቲው የምርምር፣ ህትመት፣ ስነ-ምግባር እና ኢንዳክሽን ዳይሬክተር መምህር ተመስገን ተስፋይ (ረ/ፕሮፌሰር) በበኩላቸው በጥናትና ምርምር ሂደት መምህራን ቁልፍ የምርምር መርኆች በመከተል በሃገር አቀፍ ደረጃ ተጽእኖ መፍጠር የሚችሉ፣ የማህበረሰብ ችግሮች የሚፈቱ እና ከልህቀት ማዕከላት ጋር ትስስር ያላቸው መሆን እንደሚገባቸው እንዳለባቸው ሙያዊ ማብራሪያቸውን ሰጥተዋል፡፡
ከመምህራን ጋር በተደረገ ውይይት መሰረት በጥናትና ምርምር ሂደት የተሳታፊዎችን መብትና ደህንነት የጠበቀ፣ የጥናትና ምርምር ምንጮች በአግባቡ የገለጸ እንዲሁም የማህበረሰቡን ችግር የሚፈታ ጥናትና ምርምር መሰራት እንደሚገባ ተገልጿል፡፡
የዩኒቨርሲቲው አካዳሚክ፣ ምርምር፣ ቴክኖሎጂ ሽግግር እና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕረዚደንት ዶ/ር ነጋ ዓፈራ ባደረጉት ንግግር እንዲህ አይነት መድረኮች መፈጠራቸው በተለያየ ደረጃ በሚማሩ ተማሪዎች፣ በሲኒየር መምህራንና ተመራማሪዎች የምርምር መርኆች እና ስነ ምግባር ዙሪያ እውቀትና ልምድ ልውውጥ በማድረግ፣ የምርምር መርህን በመከተል ለማህበረሰቡ ጠቃሚ ጥናትና ምርምር ማድረግ ይረዳል ብለዋል።
በሌላ በኩል መምህራን ለሚሰሯቸው የምርምር ስራዎች ተቋማዊ የሆኑ የምርምር መርኆች አክብረው መስራት እንደሚገባቸው እና ይህም በየትኛውም የምርምር ጭብጥ ላይ ጥናትና ምርምሮችን በጥራት እንዲሰሩ ያስችላል በማለት ገልጸዋል፡፡

ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታህስስ 03 ቀን 2017 ዓ.ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ሥራ አስፈፃሚ
****************************************