የዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ በማይጨው ከተማ የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል

ራያ ዩኒቨርሲቲ ከማይጨው ከተማ አስተዳደር እና ማዘጋጃ ቤት ጋር በመተባበር የዩኒቨርሲቲው ሰራተኞች የጥምቀት በዓል ምክንያት በማድረግ ዛሬ ቅዳሜ ታህሳስ 05/2017 ዓ/ም በከተማዋ የተለያዩ አከባቢዎች የፅዳት ዘመቻ አካሂደዋል።
የዩኒቨርሲቲው አስተዳደር እና ልማት ምክትል ፕረዚደንት ክብሮም ካሕሱ (ዶ/ር) በፅዳት ዘመቻው ባስተላለፉት መልእክት የጥምቀት በዓል በማይጨው ከተማ በድምቀት ስለሚከበር ከተማዋ ፅዱ እና አረንጓዴ ለማድረግ እና የከተማዋ ነዋሪ ለማነቃቃት ነው በማለት የፅዳት ዘመቻው በቀጣይ ከከተማዋ የሚለማ ቦታ ተረክበን እናለማለን ብለዋል።
የማይጨው ከተማ ከንቲባ አቶ የማነ ንጉስ በበኩላቸው ራያ ዩኒቨርሲቲ ከመማር ማስተማር በተጨማሪ በከተማዋ የልማት ስራዎች እየሰራ መምጣቱን ገልፀው የዚህም ማሳያ የከተማዋን ነዋሪ ለማነቃቃት እና አርአያ ለመሆን ታህሳስ 06/2016 ዓ/ም በዩኒቨርሲቲው ማህበረሰብ የተደረገ የፅዳት ዘመቻ አመስግነዋል።
በፅዳት ዘመቻው የዩኒቨርሲቲው አመራሮች፣ መምህራን፣ አስተዳደር ሰራተኞች እና የማህበራት ተሳትፈዋል።

ራያ ዩኒቨርሲቲ ፤ ታህሳስ 05/2017 ዓ/ም
ዕውቀት ለማኅበረሰባዊ ለውጥ!!!
የህዝብና ዓለም አቀፍ ግንኙነት ስራ አስፈፃሚ
*************************************